ከማህበረሰብ ተኮር አመቻቶች ጋር መጭው የመስቀል...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ከማህበረሰብ ተኮር አመቻቶች ጋር መጭው የመስቀል ደመራ ፣ የኢሬቻ አከባበርና የመንግስት ምስረታ አስመልክቶ እየተደረገ ያለው ውይይት በክ/ከተሞች ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።

ከማህበረሰብ ተኮር አመቻቶች ጋር መጭው የመስቀል ደመራ ፣ የኢሬቻ አከባበርና የመንግስት ምስረታ አስመልክቶ እየተደረገ ያለው ውይይት በክ/ከተሞች ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።

የከተማውን የሚመጥን የሰላም የጸጥታ የደህንነት ስራዎች ሀይማኖታዊና ብሔራዊ በዓላት ፍጹም ሰላም ሆነው እንዲያልፉ በትኩረት እየተሰራ ሲሆን በከተማው ውስጥ ካሉ ብሎክ አመቻቾች ጋር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ መጭው የመስቀል ደመራ ፣ የኢሬቻ አከባበርና የመንግስት ምስረታ እንዲሁም ባለፈው በጀት ዓመት የተሰሩትን ስራዎች በተመለከተ እየተደረገ ያለው ውይይት ዛሬም ከአራት ክ/ከተሞች ከተውጣጡ አመቻቾች ጋር ቀጥሎ ውሏል።

አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የሀሳብ ልዩነቶችን በውይይት መፍታትና ሀሳቦችን በማዳበር ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት በጋራ በመቆም ኃላፊነትን መወጣት ይገባል ብለዋል።

ሀላፊው አያይዘውም በአካባቢ ማህበረሰብ የሚያጋጥሙ ዕለታዊ ግጭትን በውይይት መፍታትና ግጭቶቹ ተመልሰው እንዳይከሰቱ በማድረግ ነዋሪው ባለው ዕውቀትና አቅም በመጠቀም ወደ ሚፈለገው ልማትና ዕድገት በመጓዝ እርስ በርስ በመግባባትን የሰላም እሴትን በማዳበር ሰላማዊ ማህበረሰብና አካባቢን የሚጠብቅ ዜጋ ላይ መስራት እንደሚገባ አሳስበው ሰላም በመንግሥት ብቻ የሚፀና ሳይሆን ህብረተሰቡም የድርሻውን መወጣት ሲችል በመሆኑ የሰላም ተሳትፊነትን ማጎልበትና ከፊታችን የሚከበሩ የአደባባይ በአላት እሴታቸውን በጠበቀ መልኩ ፍፁም ሰላማዊ ሁነው እንዲከበሩ የሚያጋጥሙ የፀጥታ ችግሮችን ለፀጥታ ሀይሉ ጥቆማ በመስጠት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ም/ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ በበኩላቸው ማንኛውም የጸጥታ መደፍረስ ዋና መንስኤዎች የሚሆኑ ድርጊቶች ከብሎክ አመቻቾችና ከመላው ማህበረሰቡ የሚደበቅ ነገር እንደሌለ ገልፀው በመስከረም ወር በርካታ በዓላት ህብረተሰቡ አደባባይ በመውጣት የሚከብሩት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ብሎኮችን በጥብቅ ክትትል በማድረግ ጸረ ሰላም ሀይሎች በማጋለጥ ህዝቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ሀላፊነት እንዳለባቸው አሳስበው ከወዲሁ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የማህበረሰብ ተኮር ምክክር/ውይይት/የመስቀል ኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከርና የመንግስት ምስረታ በስኬት እንዲጠናቀቅ በተመለከተ ለውይይቱ የሚሆነውን መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት ኮማንደር ሙሉጌታ በጋሻው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ዳይሬክተር ሲሆኑ ሰላም የማህበረሰብ የጋራ ኃላፊነት ሲሆን የሚገነባውም በመተሳሰብ፣ በመከባበር፣ በመደማመጥና በጋራ ችግሮቻችንን በምክክር በመፍታት ነው። በተለይም በዓላት፣

የመስቀልና ኢሬቻ በአዲስ አበባና በመላ ሀገሪቱ በርካታ ህዝቦች የሚያሳትፉበት ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶችን የሚያሳዩ ወሳኝ ክስተቶች ስለሆኑ እነዚህ በዓላትን በመከባበር፣ በመቻቻልና በሰላም ሲከበሩ የማህበረሰብ አንድነትንና የጋራ እሴቶችን እንደሚያጠናክር ገልጸው የመንግስት ምስረታ ሂደት በሰላማዊ፣ በህጋዊና በተሳትፎ መርህ እንዲጠናቀቅ ልዩነቶችን በግጭት ሳይሆን በውይይትና በምክክር መፍታት እንደሚገባ ገለፃ አድርዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው አካባቢያቸውን ከምንጊዜውም በበለጠ መልኩ በመጠበቅ በዓላትን ለማክበር ከሌላ አካባቢ የሚመጡ ማህበረሰቦችን በመቀበል ኢትዩጵያዊ ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ፍጹም ሰላም በሆነ ኢደት በዓሉ እንዲጠናቀቅና ለቀረው ማህበረሰብም በማስተማር ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ ሀሳባቸውን ገልፀዋል ።

ውይይቱ በነገው ዕለትም ቀጥሎ እንደሚውል ለማወቅ ተችሏል ።

መስከረም 6/2019 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79