የሰላም ሰራዊቱ የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ሃ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የሰላም ሰራዊቱ የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበር የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናገሩ።

የሰላም ሰራዊቱ የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበር የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናገሩ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአዲሱ ገበያ ክላስተር የአንድ ማዕከል የምሽት የፀጥታ ስምሪት ሰጥቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ጥበቡ በመልዕክታቸው የሰላም ሰራዊቱ ከፀጥታ ሀይሉና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት የአከባቢውን ሰላምና ደህንነት በንቃት እየጠበቀ ያለበት ሁኔታ አበረታች መሆኑን ገልፀው ስምሪት ወስዶ አከባቢን መጠበቅ የሰላም ሰራዊት የዘወትር ተግባር በመሆኑ በበዓላት ወቅት በልዩ ትኩረት አከባቢን የመጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ በበኩላቸው ሀይማኖታዊ እና ህዝባዊ የአደባባይ በዓላት በሚከበርበት ወቅት የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ አጋጣሚውን የሚጠቀሙ ሀይሎች በመኖራቸው ህዝባዊ የሰላም ሰራዊቱ አካባቢውን የፀጥታ ችግሮች እንዳይከሰቱ መስራት ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በበኩላቸው የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ በዓላት በሚከበርበት ወቅት በርካታ ህዝብ የሚሰባሰብባቸው እንደመሆኑ መጠን በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ ከብሎክ ጀምሮ የምንሰራው የፀጥታ ስራ እጅግ ወሳኝነት አለው የአንድ ማዕከል ህዝባዊ የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ገልፀው ከማመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር ተናቦ መስራት እንደሚገባም ገልፀዋል።

በቀጣይ ቀናትም የፀጥታ ስምሪቱ ተጠናክሮ የማቀጥል መሆኑ ተገልጿል።

መስከረም 5 /2019

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79