የተቀናጀ የፀጥታ ስምሪት ሰላሟ ለተረጋገጠ ከተማ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የተቀናጀ የፀጥታ ስምሪት ሰላሟ ለተረጋገጠ ከተማ !

የተቀናጀ የፀጥታ ስምሪት ሰላሟ ለተረጋገጠ ከተማ !

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው ፤ ሰላም የህዝቦች በሰላም ወጥቶ መግባትና የከተማን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ ወሳኝ እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮም በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የምሽት የፀጥታ ስምሪት ተሰጥቷል።

አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አማካሪ በስምሪቱ ወቅት እንዳሉት ቢሮው ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የከተማን ሰላም የማረጋገጥ ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው የሰላም ሰራዊቱ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የአካባቢን ሰላም በመጠበቅና የመደበኛው የፀጥታ ሀይል አቅም በመሆን እየሰራ ያለበትን ሂደት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።

በተለይም በመስከረም ወር የሚከበሩ ሀይማኖታዊና ህዝባዊ የአደባባይ በአላት ሰላማዊ ሁነው እንዲያልፉ ከፀጥታ አካሉ ጋር በመቀናጀት መስራት እንዳለባቸው አቶ ጌታሁን አቅጣጫ ሰጥተዋል።

የሰላም ሰራዊቱ የአካባቢን ሰላም በማስጠበቅ አመርቂ ስራ እየሰሩና የክ/ከተማውን ሰላም እያረጋገጡ መሆኑን የገለፁት አቶ ደረጀ የንፍስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆኑ በቀጣይም የሚከበሩ በአላት ያለ ፀጥታ ስጋት እንዲከበሩ የተቀናጀ የፀጥታ ስምሪት የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል።

መስከረም 5 /2019

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79