የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላትን በሰላም መከበር...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላትን በሰላም መከበር የባህልና የሃይማኖት እሴቶችን ከማስጠበቅ ባለፈ፣ ለማህበራዊ ትስስር፣ ለመቻቻልና ለአንድነት መጠናከር ወሳኝ ሚና አላቸው።

የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላትን በሰላም መከበር የባህልና የሃይማኖት እሴቶችን ከማስጠበቅ ባለፈ፣ ለማህበራዊ ትስስር፣ ለመቻቻልና ለአንድነት መጠናከር ወሳኝ ሚና አላቸው።

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በአል ሀይማኖታዊና በህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ለማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ከፀጥታ ጥምር ሀይል ጋር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በተመለከተ ውይይት በማድረግ የስራ አቅጣጫ አስቀምጧል ።

አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ እንደተናገሩት የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ህዝብ ወደ አደባባይ ወጥቶ የሚያከብራቸው እንደመሆኑ የፀጥታና የደህንነት ስራው በበለጠ ቅንጅትና መናበብ መስራት እንደሚጠይቅ አሳስበው ጥምር የፀጥታ አካላት ከመቼውም በላይ በመቀናጀት ህዝቡን የሰላም ባለቤት ማድረግና የነቃ ስምሪት በመስጠት የሃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ መስራት እንዳለበት ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለውም በከተማው ውስጥ ሁከትና ሽብር ለመፍጠር የሚሞክሩ ፀረ ሰላም ሀይሎችንን በጥንቃቄ በመከታተልና የቅድመ መከላከል ስራ በመስራት በአላቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብረው እንዲያልፉ ጥምር የፀጥታ ግብረሀይሉ በመናበብ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዶ/ር ተፈራ ሞላ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ እንደተናገሩት የፀጥታ ስራ የሰላምና ፀጥታ አካላት ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉም ዜጋ የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ ህብረተሰቡ የሰላም ባለቤት ሆኖ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ፣ ወንጀልን ከመከላከል ባለፈ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት የሚያስፈልግ ዘላቂ የሰላም መሠረት ይገነባል ብለዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና ስራና ክህሎት ሀላፊ አቶ ልመንህ ምህረቱ በበኩላቸው እንደተናገሩት ከፊት ለፊታችን የሚከበሩት ሁለት ትልልቅ የአደባባይ በአላት ሀይማኖታዊ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ በቂ ዝግጅት የተደረገ መሆኑን ገልፀው በዚህም የሰላምና ፀጥታ አካላት ሚናቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

በመረሃ ግብሩ የፌዴራል ፖሊስ አዲስ አበባ ፖሊስ ቋሚና ፓትሮል እንዲሁም ሌሎች የፀጥታ አካላትና ተገኝተው የጋራ አቅጣጫ ወስደዋል።

መስከረም 5 /2019

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79