የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ስጋት ተከብረው እንዲያልፉ ለጥምር የፀጥታ ግብረሀይሉ የቀጣይ አቅጣጫ ተሰጠ ።
የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ስጋት ተከብረው እንዲያልፉ ለጥምር የፀጥታ ግብረሀይሉ የቀጣይ አቅጣጫ ተሰጠ ።
የፀጥታ ጥምር ግብረሀይሉ በጳጉሜ ወር አከባበር ላይ ያሳየውን ቁረጠኝነትና ቅንጅታዊ የፀጥታና የደህንነት ስራን በቀጣይ የሚከበሩ የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት አከባበር በላቀ ሁኔታ አጠናክሮ በማስቀጠል በአለም አቀፍ ደረጃ የማይዳሰስ ቅርስ የተመዘገቡና ከኢትዮጲያ አልፎ አለም አቀፍ በዓላት እንደመሆናቸው የፀጥታ ጥምር ሀይሉ በልዩ ትኩረት በቅንጅት እየሰራ ያለውን አጠናክሮ ለማስቀጠል የጋራ አቅጣጫ ወስደዋል።
ም/ኮምሽነር አበራ ሁንዴ የፌደራል ፖሊስ የፀጥታ ዋና መምሪያ ኃላፊ እንዳሉት የዘንድሮው የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በአል ልዩ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ጠቁመው የፀጥታ ግብረሀይሉን የበለጠ ቅንጅት የሚፈልግ በመሆኑ ግብረሀይሉ በመናበብና በፈጣን የመረጃ ልውውጥ ለመስራት የተጀመረውም የቅድመ ዝግጅት ስራን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ የፀጥታ ጥምር ግብረ ሀይሉ በጳጉሜ ወር አከባበር ላይ የታየውን ቁርጠኝነት በቀጣዮቹ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በአላት አከባበር ላይ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። ኃላፊው አክለውም ጥምር የፀጥታ ሀይሉ በተቀናጀና በተናበበ መልኩ በሚሰጠው ስምሪት በንቃት በመስራት በአላቱ ፍፁም ኢትዮጲያዊ ባህልን በጠበቀና ህዝባዊ አንድነትን በሚያጠናክርና ሀገራዊ እሴትን በሚያጎላ መልኩ እንዲከበር በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ በበኩላቸው የፀጥታ ጥምር ግብረሀይሉ ባለፉት ጊዚያት ያሳየውን ቅንጅት በማስቀጠል በአሉ ያለፀጥታ ስጋት ተከብረው እንዲያልፉ በተቀመጠው አቅጣጫ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
የፀጥታ ጥምር ሀይሉ ከወትሮው በበለጠ መልኩ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የገለፁት ኮማንደር ፍስሀ ጀምበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ዲይሬክተር ናቸው።
የፀጥታ ጥምር ግብረሀይሉም በአላቱ ፍፁም ሰላማዊ ሁነው እንዲከበሩ አስፈላጊውን ቅንጅትና የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያደረጉ መሆኑን ገልፀው ከእሰከ አሁኑ በበለጠ ህብረተሰቡን መአከል ያደረገ የፀጥታና የደህንነት ስራን በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
መስከረም 5 /2019
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79