የሰላም ባህልን በማስፈን የመግባባት እሴትን በማዳበር ለትውልድ የሚተርፍ ማህበረሰብ መገንባት ይገባል።
የሰላም ባህልን በማስፈን የመግባባት እሴትን በማዳበር ለትውልድ የሚተርፍ ማህበረሰብ መገንባት ይገባል።
አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ
ሀላፊው ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከማህበረሰብ ተኮር ውይይት አመቻችቶ ጋር መጭው የመስቀል ደመራ ፣ የኢሬቻ አከባበርና የመንግስት ምስረታ እንዲሁም ባለፈው በጀት ዓመት የተሰሩትን ስራዎች መሰረት በማድረግ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው።
አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በየአካባቢው የማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶች ተጠናክረው በመቀጠላቸው ህብረተሰቡ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅና የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ለከተማ ደህንነት በጋራ መቆም ተችሏል ብለዋል።
በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት ከማህበረሰብ አመቻችቶ እንደሚጠበቅ የገለጹት ሀላፊው ውይይቶች እንዲዳብሩ ማድረግ ፣ መደማመጥንና ለጋራ ዓላማ በጋራ መቆምን መልመድ ፣ የመፍትሔ አካል መሆንና መሰል ጉዳዮች ላይ እየተሰራ ያለውን አጠናክሮ ማስቀጠል እኔደሚገባ አብራርተው ህብረተሰቡ የሰላም ባለቤት ህዝብ እንዲሆን አካባቢውን ማየት ፣ ዕድል መስጠት ህዝቡ ማሳተፍ በማስቀጠል ልዩነትን በመፍታት በእኩልነት ችግሮችን በአስተውሎት በጥበብ በመመልከት አንድ በመሆን እርስ በርስ አለመግባባት ሲኖር በጋራ ትብብር ሀሳቦች በመለዋወጥ በአንድነት በፍቅር የሀገር ሰላም ማስቀጠል እንደሚገባ አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ተናግረዋል።
የማህበረሰብ ተኮር ምክክር/ውይይት/የመስቀል ኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከርና የመንግስት ምስረታ በስኬት እንዲጠናቀቅ በተመለከተ ለውይይቱ የሚሆነውን መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት ኮማንደር ሙሉጌታ በጋሻው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ዳይሬክተር ሲሆኑ ሰላም የማህበረሰብ የጋራ ኃላፊነት ሲሆን የሚገነባውም በመተሳሰብ፣ በመከባበር፣ በመደማመጥና በጋራ ችግሮቻችንን በምክክር በመፍታት ነው። በተለይም በዓላት፣
የመስቀልና ኢሬቻ በአዲስ አበባና በመላ ሀገሪቱ በርካታ ህዝቦች የሚያሳትፉበት ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶችን የሚያሳዩ ወሳኝ ክስተቶች ስለሆኑ እነዚህ በዓላትን በመከባበር፣ በመቻቻልና በሰላም ሲከበሩ የማህበረሰብ አንድነትንና የጋራ እሴቶችን እንደሚያጠናክር ገልጸው የመንግስት ምስረታ ሂደት በሰላማዊ፣ በህጋዊና በተሳትፎ መርህ እንዲጠናቀቅ ልዩነቶችን በግጭት ሳይሆን በውይይትና በምክክር መፍታት እንደሚገባ ገለፃ አድርዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሰላም የሁሉም መሰረት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለራስ ለአካባቢ ሲቀጥል ለሀገር በጋራ በመስራት ውይይቶችን በማዳበር የሰለጠነ ማህበረሰብ መገንባት እንደሚገባቸው ና ከበፊቱ በበለጠ መንገድ እንደሚተጉ ተናግረዋል።
ውይይቱ በሶስቱ ዙር የሚቀጥል ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል ።
መስከረም 5/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79