የተቀናጀ የፀጥታ ስምሪት ለሰላምና ደህንነቱ ለ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የተቀናጀ የፀጥታ ስምሪት ለሰላምና ደህንነቱ ለተጠበቀ ከተማ!

የተቀናጀ  የፀጥታ ስምሪት ለሰላምና ደህንነቱ ለተጠበቀ ከተማ!

 የፀጥታ ስምሪት  የከተማን  ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ በቅንጅትና በዕቅድ እየተከናወነ ይገኛል ። የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ  በመስከረም ወር የሚከበሩ  በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ የፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት እንዲሰሩ ስምሪት ተሰጠ።

አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ እና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ በስምሪቱ ወቅት እንደገለጹት  የፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት በመሥራታቸው በከተማው የሚከሰቱ ወንጀሎችን መቀነስ ተችሏል ብለዋል ። ይህንንም ውጤት በማጠናከር መጪዎቹ በመስከረም ወር በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ የፀጥታ ሥራውን በተጠንቀቅ መምራትና መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በተለይም በከተማዋ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በቅርበት በመከታተል፣ ሊያስከትሉ የሚችሉትን የፀጥታ ስጋት በቅድሚያ  መለየትና  በተቀናጀ አሠራር ማክሸፍ  እንደሚገባ  ኃላፊው አሳስበው ህብረተሰቡ  ለፀጥታ  ሀይሉ  አቅም በመሆንና  አላስፈላጊ  እንቅስቃሴዎች ሲያጋጥሙ ጥቆማ በማድረስ  የድርሻውን በመወጣት ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚገባም ሀላፊው ገልጿል።

አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ  እንዳሉት  የፀጥታ ጥምር ሀይሉ እስከ አሁን እየሰራ ያለበትን አግባብ አጠናክሮ በመቀጠልና በተለየ ትኩረት አካባቢን በንቃት መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የቦሌ ክ/ከተማ ም/ል ስራ አስፈጻሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አንቺነሽ ተስፋዬ  በበኩላቸው ቀንና ሌሊት፣ ፀሐይና ብርድ ሳይበግራቸው የሀገራችንን ሰላምና ፀጥታ በመጠበቅ ላይ የሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች እና የከተማችንንና የአከባቢያቸውን ሰላም  የሚጠብቁ የሰላም ሰራዊት አባላት መጪው የዘመን መለወጫና የመስከረም ወር በዓላት በሰላምና በደህንነት እንዲከበሩ በቅንጅት እየሠሩ እንደሆነና፣የፀጥታ ሥራው ውጤታማ እንደሆነ ገልፀው   ሁሉም አካላት የበኩሉን መወጣት ይገባል ብለዋል።

የተቀናጀ ስምሪት፣ የተረጋጋ ሰላም!

ጳጉሜን 4/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79