ሰላም ከእያንዳንዱ ሰው ይጀምራል! በዕውቀት፣ በ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ሰላም ከእያንዳንዱ ሰው ይጀምራል! በዕውቀት፣ በትዕግስትና በታማኝነት ሰላምን እንገንባ።

ሰላም ከእያንዳንዱ ሰው ይጀምራል! በዕውቀት፣ በትዕግስትና በታማኝነት ሰላምን እንገንባ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በተለያየ ምክንያት የተጓደሉ የሰላም ሰራዊት አባላትን በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ 2000 አጋዥ የፀጥታ አካላትን አስመርቆ የስራ ስምሪት ሰጠ።

ቢሮው ከባለፉት አራት አመታት ጀምሮ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በጎ ፈቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን በሰላም ሰራዊት በማደራጀት ከ2 መቶ ሺ በላይ የሰላም ሰራዊቶችን የንድፈ ሀሳብና የመስክ ወታደራዊ ስልጠና እየሰጠ ለመደበኛ የፀጥታ አካሉ አጋዥ እያደረገ ይገኛል። ይህን አጠናክሮ ለማስቀጠል በተለያየ ምክንያት የተጓደሉ አባላትን ለመሙላት በሁሉም ክ/ከተሞች የማካካሻ ስልጠና ለተከታታይ አስር ቀናት አሰልጥኖ ወደ ስራ ያስገባ ሲሆን ዛሬም በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ሁለት ሺህ የሰላም ሰራዊት አስመርቆ ወደ ስራ አስገብቷል።

አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በምረቃ መርሐግብሩ ላይ ተገኝተው እንዳሉት ተመራቂዎች ሰላምን በመገንባት ፣ የአካባቢን ሰላም በማፅናትና የሰላም እሴትን በማጎልበት ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በኃላፊነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

አቶ ፍሰሀ አክለውም ሀገራችን ሰላም የሰፈነባት ዕድገትና ብልፅግናዋ የተረጋገጠባት እንደመሆኗ ይህን አጠናክሮ ማስቀጠልና ከተማችን አዲስ አበባም ሰላሟ የተረጋገጠባት ህዝቦቿ በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ብሎም በከተማችን የተጀመሩ የልማትና የተለያዩ ተግባራት በውጤታማነት እንዲጠናቀቁና አንዳንድ የሚያጋጥሙ የፀጥታ ስጋቶች በመለየት የቅድመ መከላከል ስራዎችን በመስራትና ለመደበኛው የፀጥታ አካላት አቅም በመሆን አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ አፅንኦት ሰጥተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ አከበረኝ ወጋገን የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ም/ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ እንዳሉት በ2018 ዓ.ም የተሰሩ የፀጥታና የአካባቢን ሰላም የማስከበር ስራ ውጤታማ መሆኑን አንስተው ዛሬ ስልጠና ወስደው ወደ ስራ የሚገቡ አጋዥ ሀይሎች በሚሰጣቸው ስምሪት ከመደበኛ የፀጥታ አካሉ ጋር በቅንጅት በመስራት ከፊታችን የሚከበሩ ሀይማኖታዊና ህዝባዊ በአላት ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲያልፉ በቅንጅት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

ፀጥታን ማረጋገጥና ማስቀጠል የሚቻለው በአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን በህብረተሰቡ ቅንጅታዊ ተሳትፎ ነው ያሉት የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ሀይሉ ሲሆኑ በቀጣይም የሰላም ሰራዊቱ ለመደበኛ የፀጥታ አካሉ የመረጃ ምንጭ በመሆንና አጋዥ በመሆን የከተማን ሰላም ማስጠበቅ በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ተመራቂ የሰላም ሰራዊቱ የቃለ መሀላና የስራ ስምሪት ተሰጥቷል።

ጳጉሜን 4/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79