የዘመን መለወጫ፣ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ ክብረ በዓላት ሰላማዊ አከባበር ላይ የፀጥታ ስጋት ልየታ ትኩረት ተሰጠ።
የዘመን መለወጫ፣ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ ክብረ በዓላት ሰላማዊ አከባበር ላይ የፀጥታ ስጋት ልየታ ትኩረት ተሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ መረጃ ዘርፍ የዘመን መለወጫ፣ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ ክብረ በዓላት ሰላማዊና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እንዲከበሩ የተዘጋጀውን የፀጥታ ስራዎች ማስፈጸሚያ ዕቅድ እና የፀጥታ ስጋት ሁኔታ ልየታን በተመለከተ አጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ዙሪያ አካሂዷል።
በዓላቱ ብዙ ህዝብ የሚሳተፍባቸው በመሆናቸው የህዝብ እንቅስቃሴ፣ የመጨናነቅ ሁኔታ፣ የትራፊክ ፍሰትና ሌሎች የፀጥታ ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ሁኔታዎችን በቅድሚያ መለየትና ተገቢውን የመፍትሄ ርምጃ ማስቀመጥ፣ከኢኮኖማና ከዋጋ ንረት አኳያ በደንብ መሥራት እንደሚገባና የበዓላቱ ሰላማዊ አከባበር የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ስራና ትብብርን የሚጠይቅ በመሆኑ፣ የፀጥታ መረጃ በቅንጅት በመሰብሰብ፣ በመተንተንና በመጠቀም የበዓላቱን ሰላማዊና ደህንነቱ የተጠበቀ አከባበር ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ዶ/ር ወንድማገኝ ታደሰ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ኃላፊና የመረጃ ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ፣ በመድረኩ ተናግረዋል።
በበዓላቱ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ የፀጥታ ስጋቶችን አስቀድሞ በመለየት፣ በመተንተንና ተገቢውን የመከላከያ እርምጃ በመውሰድ የበዓላቱን ሰላማዊ አከባበር ማረጋገጥ ላይ እና በተለይም የፀጥታ ስጋት ሁኔታዎችን በወቅቱ መለየት፣ ትክክለኛና የተረጋገጠ የፀጥታ መረጃ ማሰባሰብ፣ መረጃን መተንተንና ለሚመለከታቸው አካላት በወቅቱ ማድረስ የፀጥታ ስራውን በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ ለማስፈጸም ወሳኝ መሆኑ ሰነዱን ያቀረቡት አቶ አስፋው አለሙ የዘርፉ የቅድመ ማስጠንቀቅያና ፈጣን ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመድረኩ አቅርበዋል።
በተጨማሪም ወ/ሪት ዳግማዊት ቸርነት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ መረጃ ዘርፍ፣የፀጥታ መረጃ አስተዳደር የክትትል ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመስከረም ወር የሚከበሩት የዘመን መለወጫና የመስቀል ደመራ በዓላት ሰላማዊና ደህንነቱ በተጠበቀና ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር፣ጥራት ያለውና ቀልጣፋ የፀጥታ መረጃዎችና ቅብብሎሾች፣በፀጥታ አሰተዳደርና በመረጃ አካላት፣በመረጃ ምንጮች መካከል የፀጥታ ችግር እንዳይኖር ህብረተሰቡን በማሳተፍ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ፣ሰጋት የሆኑ አከባቢዎችን በመለየት ከጸጥታ ስጋት ነጻ እንዲሆኑ በማድረግ፣ክብረ በዓላቱን በማስመልከት ሊከሰቱ የሚችሉ የኢኮኖሚ አሻጥርና ምክንያታዊ ያልሆኑ የዋጋ ጭማሪ መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል ማስፈጸሚያ ዕቅድ ውይይት በመድረኩ አብራርተዋል።
በመድረኩ ከማዕከልና ከአስራንዱም ክ/ከተሞች የዘርፉ አስተባባሪዎች፣ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን፣ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
ጳጉሜን 3/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79