የፅናት ቀን! በጀገኖቿ መስዋዕትነት የጸናች፣ የማትደፈር ኢትዮጵያ!
የፅናት ቀን! በጀገኖቿ መስዋዕትነት የጸናች፣ የማትደፈር ኢትዮጵያ!
ልዩ የደም ልገሳ መርሐ ግብር ተካሄደ።
የ2018 ዓ.ም የጳጉሜ ወር በተለያዩ ስያሜዎች የሀገርን ከፍታ በሚያሳይና በሚያጋግጥ መልኩ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዛሬው ዕለትም ጳጉሜ 3 የፅናት ቀንን በማስመልከት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ አስተዳደር በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮምሽን ጋር በጋራ በመሆን የደም ልገሳ መርሐ ግብር አክብረዋል።
አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ በደም ልገሳ መርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት በፅናት የቆመች ሀገርን በሉአላዊነትና በጀግንነት በማገልገል ደማቸውን አፍስሰው ሀገር እንደ ሀገር እንድትፀና ላስቻሉ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊትና ለፀጥታ አካላት በተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ደም ለሚያፈልጋቸው ዜጎች እንዲውል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀው ይህም አብሮነትን የሚያጠናክር በልዩነቶች ውስጥ መቀራረብና አንድነትን በማጠናከር የፀናች ሀገርን ለማቆየትና ህዝቦቿ እርስ በስር ተከባብረውና ተጋምደው የሚኖሩባት ኢትዮጲያን ለማፅናት የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጲያ በፅናት የቆመች ሀገርና ለብዙ ሀገራት ምሳሌ የሆነች የአንድነትና የፍቅር ተምሳሌት እንደመሆኗ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በአብሮነት በመሻገር የኢትዮጵያን ልዕልና ማረጋገጥ እንደሚገባ በደም ልገሳው ላይ ተገልፃል፡፡
ጳጉሜን 3/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79