የፀጥታ ጥምር ሀይሉ በሚሰጠው ስምሪት በንቃትና በቅንጅት የአካባቢንና የከተማን ሰላም የማረጋገጥ ስራ እየሰራ ይገኛል።
የፀጥታ ጥምር ሀይሉ በሚሰጠው ስምሪት በንቃትና በቅንጅት የአካባቢንና የከተማን ሰላም የማረጋገጥ ስራ እየሰራ ይገኛል።
ከአዲስ አመት መምጣት ጋር ተያይዞ የሚከበሩ የአደባባይ ሀይማኖታዊ ፣ ህዝባዊና መንግስታዊ በአላት ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ ለጥምር የፀጥታ ሀይሉ ስምሪት ተሰጥቷል።
አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በስምሪት አሰጣጡ ላይ እንዳሉት የፀጥታ ጥምር ሀይሉ እስከ አሁን እየሰራ ያለበትን አግባብ አጠናክሮ በመቀጠልና በተለየ ትኩረት አካባቢን በንቃት መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
ም/ቢሮ ኃላፊው አክለውም የፊታችን መስከረም ወር የሚከበሩ የአደባባይ በአላት ያለምንም ፀጥታ ስጋት ተከብረው እንዲያልፉና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶችን የቅድመ መከላከል ስራዎችን በመስራት ሰላሟ የተረጋገጠባት ከተማና በአላቱ ትውፊታቸውን ጠብቀው ያለፀጥታ ስጋት እንዲያልፉ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
ጥምር የፀጥታ ሀይሉ በተሰጠው ስምሪት በነቃት እንደሚሰሩ የገለፁ ሲሆን በስምሪቱ ላይ የቢሮ ም/ኃላፊውን ጨምሮ የአራዳ ክ/ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ ሙሉነህን ጨምሮ የክ/ከተማው የፖሊስ አዛዦችና አመራሮች የተገኙ ሲሆን ስምሪቱ በሌሎች ክ/ከተሞችም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79