መጭዎቹ የአደባባይ ሀይማኖታዊ ፣ ህዝባዊና መንግ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

መጭዎቹ የአደባባይ ሀይማኖታዊ ፣ ህዝባዊና መንግስታዊ በአላት ያለፀጥታ ስጋት ለፀጥታ ጥምር ሀይሉ ስምሪት ተሰጠ።

መጭዎቹ የአደባባይ ሀይማኖታዊ ፣ ህዝባዊና መንግስታዊ በአላት ያለፀጥታ ስጋት ለፀጥታ ጥምር ሀይሉ ስምሪት ተሰጠ።

በመስከረም ወር የሚከበሩ የአደባባይ ሀይማኖታዊ ፣ ህዝባዊና መንግስታዊ በአላት ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲያልፉ በተኩረት መሰራት ስላለባቸው የፀጥታና የደህንነት ስራዎች ለለሚኩራ ክ/ከተማ ጥምር የፀጥታ ስምሪት የተሰጠ ሲሆን በስምሪቱ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድርና የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራን ጨምሮ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

የፀጥታ ጥምር ሀይሉ የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራ ላይ ትኩረት በማድረግ በቅንጅት አካባቢን መጠበቅና በአላቱ ይዘታቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲከበሩ በንቃት መጠበቅ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር አሳስበዋል።

በበአላት ወቅት ከወትሮው በበለጠ መልኩ የፀጥታና የደህንነት ስራዎች እጅግ በተናበበና በተቀናጀ መልኩ መስራት ይጠበቃል ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ጥምር ሀይሉ በተሰጠው ተልዕኮ መሰረት አካባቢን ብሎም የከተማውን ሰላም የማስጠበቅ ሂደትን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የፀጥታ ስራ የሁልጊዜ ተግባር ነው ያሉት የለሚኩራ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ ተስፋዬ ጥምር ሀይሉ እንደሁልጊዜው አካባቢውን የመጠበቅ ስራ የሚሰራ መሆኑንና መጭዎቹ በአላትም በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ለፀጥታ መዋቅሩ ለስራ የሚውል የቁሳቁስ ድጋፍ ተበርክቷል።

ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79