የሀይማኖታዊና ህዝባዊ የአደባባይ በዓላት ፍፁም...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የሀይማኖታዊና ህዝባዊ የአደባባይ በዓላት ፍፁም ሠላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ ለማስቻል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ መሆናቸው ተገለፀ።

የሀይማኖታዊና ህዝባዊ የአደባባይ በዓላት ፍፁም ሠላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ ለማስቻል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ መሆናቸው ተገለፀ።

በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የፀጥታ ግብረሀይል የሀይማኖትና የአደባባይ ክብረ በዓላት በሠላም እንዲጠናቀቁ በሚያስችሉ እቅዶች ዙሪያ ከግብረ ሀይሉ አባላት ጋር ውይይት አካሄዶ የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል ።

በዚህም የበዓላቱ አከባበርና የፀጥታና የደህንነት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ ግብረ ሀይሉ ውይይት ያደረገ ሲሆን በዓላቱ በሰላም፣ በደመቀ እና መንፈሳዊ ወይም ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲያልፉ የፀጥታ ጥምር ሀይሉ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ደንድር የሀይማኖታዊ እና የአደባባይ በዓላት ለማህበረሰባችን ከፍተኛ ማህበራዊ፣ ባህላዊ እና መንፈሳዊ እንዲሁም የአንድነት፣ የፍቅር፣ የመቻቻል እና የአብሮነት እሴቶችን የምናጎለብትባቸው አጋጣሚዎች በመሆናቸው በዓላቱ በሰላም፣ በሥርዓት እና በከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ እንዲከበሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ መልኩ መሥራት ይገባል ብለዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ልመንህ ምህረቱ በበኩላቸው የበዓላቱ ሰላማዊ አከባበር የመንግሥት ወይም የጸጥታ አካላት ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ያሉት አቶ ልመንህ በየደረጃው ያሉ የህብረተሰብ ክፍል ህግን በማክበር ለሰላም የሚያበረክቱ ተግባራትን በመፈጸም የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79