የሰላም ሰራዊትና የጸጥታ ጥምር አባላት ከፊታችን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የሰላም ሰራዊትና የጸጥታ ጥምር አባላት ከፊታችን የሚከበሩ በዓላት ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ ዝግጁነታቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለፀ።

የሰላም ሰራዊትና የጸጥታ ጥምር አባላት ከፊታችን የሚከበሩ በዓላት ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ ዝግጁነታቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለፀ።

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የሰላም ሰራዊት አባላትና የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እንዲሁም የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ ጋቸና ሲርና በተገኙበት የተቀናጀ የአንድ ማዕከል የፀጥታ ስምሪት በተደራጀ መልኩ ተሰጥቷል።

በስምሪቱ ወቅት የተገኙት የአዲስ አበባ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ዋና አማካሪ አቶ ጌታሁን አበራ እንደገለፁት የጳጉሜ ቀናትን ጨምሮ መጪው አዲስ ዓመት ህዝባዊና የአደባባይ በዓላት የሚከበሩበት በመሆኑ በዓላቱ ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ የሰላም ሰራዊትና መላው የፀጥታ አካላት በተቀናጀ ሁኔታ የጀመሩትን ስራ ማጠናከር አለባቸው ብለዋል።

አቶ ጌታሁን አክለው የህዝብን ተሳትፎ በማሳደግ ማህበረሰቡን በፀጥታ ስራ ላይ ባለቤት ማድረግ ስራዎች መጠናከር እንደሚገባም ገልፀዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አከበረኝ ወጋገን በበኩላቸው በሁሉም ወረዳዎች የሚገኙ የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የአካባቢያቸውን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ተግባር በግንባር ቀደምትነት እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል።

ከፊታችን የሚከበሩ በዓላት ሰላማዊ እንዲሆኑም የተቀናጀ የፀጥታ ስምሪቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የክፍለ ከተማው ወረዳ 07 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ቱሉ በአንድ ማዕከል የሚሰጡ የተቀናጁ የፀጥታ ስምሪቶች ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው አብራርተዋል።

በዚህ የተቀናጀ የአንድ ማዕከል የፀጥታ ስምሪት መርሃ-ግብር ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የሰላም ሰራዊት፣ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች፣ ጋቸና ሲርና እና ሌሎች የፀጥታ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።