ባለፈው በጀት ዓመት የተገኙ የሰላም የጸጥታና የደህንነት ስራዎች በመጭው አመትም አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ።
ባለፈው በጀት ዓመት የተገኙ የሰላም የጸጥታና የደህንነት ስራዎች በመጭው አመትም አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ።
አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አማካሪ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ባለፈው በጀት አመት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በወጭው ዓመትም የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል በዛሬው ዕለት ከሀይማኖት አባቶች ፣ ከተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ከወጣቶች፣ከህብረተሰብ ተወካዮች፣እና ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ውይይትና ምክክር አድርጓል።
አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አማካሪ በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው ባለፈው በጀት ዓመት የከተማውን ሰላም ደህንነት የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የከተማው የልማት ስራዎች በፈጣን እንቅስቃሴዎች ተጀምረው እንዲጠናቀቁ ከማድረግ አንጻር በርካታ ስራዎች መሰራታቸው ገልፀዋል ።
ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የተለያዪ አደረጃጀቶችን ከጸጥታው ሀይልና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ነዋሪውን በማቀናጀት አስተማማኝ ሰላም ማምጣት እንደተቻለም ያስታወሱት አማካሪው የወንጀል ምጣኔ የቀነሰበት ዋናው ምክንያትም ህብረተሰቡ ስለ ሰላም በያገባኛል ስሜት ሀላፊነቱን ስለተወጣም እንደሆነ ጠቁመው በቀጣይም መላው ህብረተሰብ በጋራ የመስራት ሂደትን አጠናክሮ ማስቀጠል አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ያሸነፈችበትንና የመከረችበት በከተማው ላይ የሚከናወኑ ጉዳዮች በሙሉ በሰላምና በድል የተጠናቀቀበት በቀጣይም የመንግስት ምስረታ የሚጀመርበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሀገርን ዕድገትና ብልጽግና የማይፈልጉ በርካታ አካላትን በትኩረት በመቆጣጠር ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ቀጣይነት ያለው ሰላም ማረጋገጥ ከመላው ነዋሪ ይጠበቃል ሲሉ ተደምጠዋል።
አቶ ማስረሻ ሀብቴ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የዕቅድና በጀት ዳይሬክተር ሲሆኑ በቀጣይ አመት ቢሮው ትኩረት አድርጎ መስራት የሚያስችላቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ገለጻ ያደረጉት ሲሆን በዋናነት የሰላም የጸጥታ ስራ ላይ ተሳትፊን ማጎልበት ፣ ሰው ተኮር ተግባራት ላይ ተሳትፎ ማድረግ ፣ ሀይማኖታዊ ብሔራዊ የአደባባይ በዓላት ፍጹም ሰላማዊ ሆነው እንዲያልፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲወጡ፣ የጸጉረ ልውጥና የጸረ ሽብር ሀይሎችን መከላከያና ማጋለጥ የሚሉት በዋነኝነት ተጠቅሰዋል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሀገር ሰላም ማጣት ሁሉም ማህበረሰብ ላይ ተጽዕኖ ስለሚኖር በየቤተ እምነታቸውና በየአካባቢያቸው ለህብረተሰቡ በማስተማር ሀገር ተረካቢ ትውልድና ዜጋን ለማፍራት በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ነሀሴ 28/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79