የአደባባይ በአላት ፍፁም ሰላማዊ ሁነው እንዲያልፉ የፀጥታ ግብረሀይሉ በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።
የአደባባይ በአላት ፍፁም ሰላማዊ ሁነው እንዲያልፉ የፀጥታ ግብረሀይሉ በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከፊታችን የሚከበሩ የአደባባይ በአላት ሀይማኖታዊ ይዘታቸውን ጠብቀው ፍፁም ሰላማዊ ሁነው እንዲያልፉ በቦሌ ክ/ከተማ የፀጥታ ጥምር ሀይል ጋር ውይይት አካሂዷል።
የፀጥታ ግብረ ሃይሉ ከፊታችን ከሚከበሩ በዓላት ጋር ተያይዞ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ገምግሞ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጧል።
ዶ/ር ወንድማገኝ ታደሰ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት በመስከረም ወር የሚከበሩ የአደባባይ በአላት ሰላማዊ በሆነ መልኩ ሀይማኖታዊ ይዘታቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲከበሩ የፀጥታ ጥምር ሀይሉ ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
ኃላፊው አክለውም የማስፈፀሚያ ዕቅዱን መሰረት በማድረግ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚጠበቅና ከፀጥታ ስጋት ነፃ ሆኖ እንዲከበር ማስቻል ይጠበቃል ብለዋል ።
ነሀሴ 27/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79