ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የከተማዋን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የከተማዋን ሰላም በዘላቂነት ለማፅናት የሚደረገው የምሽት ስምሪት አመርቂ ውጤት እያስገኘ ነው ።

ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የከተማዋን ሰላም በዘላቂነት ለማፅናት የሚደረገው የምሽት ስምሪት አመርቂ ውጤት እያስገኘ ነው ።

በአዲስ አበባ ከተማ የምሽት የፀጥታ ስምሪት አሰጣጥን የድሬደዋ ከተማ የፀጥታ ልዑክ ልምድ የወሰደ ሲሆን ልዑክ ቡድኑ አጋዥ የፀጥታ ስምሪቱ የስምሪት አቀባበልና የመረጃ ልውውጥ ሂደትን ተመልክተዋል።

አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት በአዲስ አበባ ከተማ ከ2 መቶ ሺ በላይ የሰላም ሰራዊት በማደራጀት የአካባቢን ሰላም በመጠበቅና ከመደበኛ የፀጥታ ሀይሉ ጋር በጋራ በመሆን የከተማን ሰላም ለማረጋገጥ አጋዥ ሀይል በማድረግ በከተማዋ የወንጀል ምጣኔ እንዲቀንስ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ማህበራትን በማደራጀት ማለትም የጫኝና አውራጅ ፣ የቅጥር ጥበቃና የታክሲ ተርሚናል ተራ አስከባሪዎችን ወደ ስራ በማሰማራት ህብረተሰቡን ካላስፈላጊ ወጭ መታደግ ተችሏል ያሉት ቢሮ ኃላፊው ቢሮው የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት እንዲችል የተደራጀው የሰላም ሰራዊትና የተደራጁ ማህበራት ከፍተኛ ድርሻ አላቸው ብለዋል።

አቶ ዮናስ ጠገነ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ አማካሪ በበኩላቸው አዲስ አበባ ከተማ የኢትዮጲያውያን የጋራ ከተማ እንደመሆኗ የከተማዋን ስም በሚመጥን መልኩ በሰላም ማስጠበቅ ረገድ ቢሮው ከህብረተሰቡ ጋር እየሰራ ያለበት ሂደት የሚመሰገን ነው ብለዋል።

ቡድኑ በቢሮው የተመለከቱት የአሰራር ሂደት የሚመሰገንና ጥሩ ልምድ ያገኙበት መሆኑን ገልፀዋል።

ነሀሴ 25/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79

S