የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለድሬደዋ ከተማ አቻው ልምድ አካፈለ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለድሬደዋ ከተማ አቻው ልምድ አካፈለ።
የልምድ ልውውጥ በፀጥታ ስራ የተሻሉ ተሞክሮዎችን ለመውሰድ ፣ ለመቀራረብ፣ ጠንካራ አሰራሮችን ለማስፋትና ወንጀል ድንበር የለሽ እንደመሆኑ የወንጀል መንስኤዎች ቀድሞ በመለየት ሰላማዊ ከተማን ለመገንባት ከፍተኛ አበርክቶ አለው።
ቢሮው የሚሰራበትን የአሰራር ይዘትና በተለይም ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ እየሰራበት ያለውን የወንጀል መከላከልና የፀጥታና የደህንነት ስራ ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ተቋም ለመጡ ልዑካኖች ያካፈለ ሲሆን ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ውጤታማ ስራ ማስመዝገብና በከተማዋ የወንጀል ምጣኔን መቀነስ መቻሉ በልምድ ልውውጥ ተመላክቷል።
ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የመጡት የፀጥታ ልዑካን ቡድኖችም በቢሮው የተመለከቱት የፀጥታ አጠባበቅ ሂደት ፣ ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት የሚሰራበት አግባብ ፣ የወንጀል መከላከልና ቅንጅታዊ ስራዎችን ተሞክሮ በቀጣይ ስራቸው አቅም እንደሚሆናቸው ገልፀዋል።
ነሀሴ 25/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79