በቀጣይ 5 ዓመታት የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ በትኩረት ይሰራል
በቀጣይ 5 ዓመታት የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ በትኩረት ይሰራል
ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም
በቀጣይ 5 ዓመታት የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ በትኩረት እንደሚሠራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2019 በጀት ዓመት እና በቀጣይ 5 ዓመታት እቅዶች ላይ ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት አምስት ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች ትኩረት ሰጥቶ ያከናወናቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትንም ገምግሟል፡፡
በግምገማ መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለጹት፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በሰላምና ፀጥታው ዘርፍ ከነዋሪው ጋር በመቀናጀት በተሰራው ስራ በከተማዋ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም መገንባት ተችሏል፡፡
ኃላፊዋ አክለውም ባለፉት ዓመታት የወንጀል ሥጋትን በ47 በመቶው መቀነስ መቻሉን ጠቅሰው፣ በቀጣይ አምስት ዓመታት ደግሞ የወንጀል ሥጋትን ወደ 20 በመቶው ለመቀነስ ሰፊ እቅድ ተይዞ ወደ ስራ መገባቱን ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡
የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮዎችን ጨምሮ፣ ሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት በተገኙበት እየተካሄደ ባለው በዚህ የግምገማ መድረክ፣ በቀጣይ አምስት ዓመታት የህዝብን ጥያቄዎች በተሻለ መንገድ ለመመለስ የሚያስችሉ ዝርዝር እቅዶች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ተመላክቷል፡