በተጓደሉ የሰላም ሰራዊት አባላት ማሟያ በንድፈ ሀሳብና ወታደራዊ የመስክ ስልጠና የተግባር ማነቃቂያ የተጀመረው ስልጠና ቀጥሏል።
በተጓደሉ የሰላም ሰራዊት አባላት ማሟያ በንድፈ ሀሳብና ወታደራዊ የመስክ ስልጠና የተግባር ማነቃቂያ የተጀመረው ስልጠና ቀጥሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በ2019 በጀት አመት በተጎደሉ የሰላም ሰራዊት አባላት ማሟያ በንድፈ ሀሳብና ወታደራዊ የመስክ ስልጠና የተግባር ማነቃቂያ ስልጠና በኮልፊ ቀራንዩ ክ/ከተማ በዛሬው ዕለት መስጠት ጀምሯል።
በማስጀመሪያው መርሐ ግብሩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ደሳለኝ ሀይሉ የኮልፌ ክ/ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ ሲሆኑ ሰላም ትልቅ ሚና ያለው ሀገር ለመገንባት ሰላም እንዲሰፍን ዋናው የሰላሙ ባለቤትም ህዝቡ ስለሆነ በተገቢው መንገድ ስልጠናውን በመከታተልና ህዝቡን በማገልገል አካባቢውን የሚጠብቅ ለሰላም አቅም መፍጠር የሚችል የሰላም ሰራዊት አቅም የሚፈጥር ስልጠና ስለሆነ በትኩረት ማየትም ይገባል ብለዋል።
በሰላም ሰራዊቱ ምክንያት የወንጀል ስጋት የነበሩ ቦታዎች ስጋቱ የቀነሰበት በሰራዊቱ ምክንያት ነዋሪው በሰላም ወቶ መግባት የቻለበት ዋጋ የተከፈለበት ስለሆነ ሰላም የመጣበት ስለሆነ ሀላፊነትን በአግባቡ መወጣት ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።
ኮምሽነር ሞቱማ ሲማ የክ/ከተማው ፖሊስ መምሪያ ዋጋ አዛዥ በበኩላቸው መንግስት የሰጠንን ሀላፊነት በተገቢው መንገድ እየተወጣን እንገኛለን በማለት ጸረ ሽብር ሀይሎችንና ጸጉረ ልውጦችን በመለየት በህገወጥ መንገድ ስራዎችን የሚሰሩ ግለሰቦች ስላሉ እሱን አጥብቆ በተቻለ መጠን ሁሉ በጥብቅ በመስራት የወንጀል ምጣኔን መቀነስ እንደተቻለ አብራርተው የሰላም ሰራዊቱ አደረጃጀት ብርቱ ስለሆነ በቀጣይ ተቀናጅቶ በመንቀሳቀስ ከፊታችን የሚከበሩ በርካታ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲያልፍ በማድረግ ትልቅ ሚና እንድትወጡ አደራ እላለሁ ሲሉ ተደምጠዋል ።
ስልጠናው ለተከታታይ አስር ቀናት በወታደራዊ መስክ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል።
ነሀሴ 25/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79