ትስስርና ቅንጅት ለተሻለ የሰላምና ፀጥታ ሥራ!
ትስስርና ቅንጅት ለተሻለ የሰላምና ፀጥታ ሥራ!
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት ህብረተሰቡን የሚያሳትፍ ዕቅድ በማቀድ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ይህን መሰረት በማድረግም በርካታ የፀጥታና የደህንነት ስራዎች ፣ የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎችን ከነዋሪውና ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።
የቢሮውን ተልዕኮ በላቀ አፈፃፀም ተግባራዊ ለማድረግና የተሰጠውን ተግባር ለማሳካት በስሩ የሚገኙ የአላማ ፈፃሚና የደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች በጋራ ለመስራት የሚያስችል የውል ስምምነት ተፈራርመዋል።
አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አማካሪ እንዳሉት የሰላምና ፀጥታ ሥራ የአንድ ተቋም ወይም የአንድ አካል ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉም የጋራ ተልዕኮ በመሆኑ ተቋማትና የሥራ አጋሮች ጠንካራ ትስስር በመፍጠር በጋራ መስራት ሲችሉ የሰላምና ፀጥታ ሥራ የተሻለ ውጤት የሚያስገኝ መሆኑን ገልፀው በውሉ መሰረት በየወሩ ስራዎችን መገምገምና ለተሻለ አፈፃፀም ማምጣት ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።
ዕቅዶችን በቅንጅት መሥራት የመረጃ ልውውጥን ያጠናክራል፣ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያስችላል፣ ሀብትና አቅምን በተገቢው ሁኔታ ለመጠቀምና የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎችን ያግዛል ስለሆነም ዛሬ በተዋዋሉት መሰረት ስራዎቹን እንደሚሰሩ የገለፁት ዳይሬክቶሬቶቹ በቀጣይ ተግባራትን አስተሳስረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ችግሮችን በጋራ በመፍታት ዘላቂ ሰላምና የተረጋጋ ፀጥታ ለማረጋገጥና የህግ የበላይነትን ለማስፈን በቅንጅት እንደሚሰራ ተመላክቷል።
ነሀሴ 22/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157