የተጠናከረ የፀጥታ ስምሪት በመስጠት፣ ቅድመ መከ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የተጠናከረ የፀጥታ ስምሪት በመስጠት፣ ቅድመ መከላከልን በማጠናከር እና ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት በመስራት የተረጋጋና ሰላማዊ አካባቢ መፍጠር መቻሉ ተገለፀ።

የተጠናከረ የፀጥታ ስምሪት በመስጠት፣ ቅድመ መከላከልን በማጠናከር እና ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት በመስራት የተረጋጋና ሰላማዊ አካባቢ መፍጠር መቻሉ ተገለፀ።

የሀገርን ብሎም የከተማን ሰላም ማስጠበቅ የጋራ ኃላፊነት ቢሆንም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግና የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎችን እየሰራ የከተማውን ሰላም  በማስጠበቅ  የነዋሪዎቿን በሰላም ወጥቶ መግባት እያረጋገጠ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በልደታ ክ/ከተማ የአንድ ማዕከል የፀጥታ የሰላም ሰራዊት ስምሪት ሰጥቷል።

አቶ ፍስሀ ጥበቡ የቢሮው ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በስምሪቱ ላይ ተገኝተው እንዳሉት  የፀጥታ ጥምር ሀይል የምሽት ስምሪት አየተሰጠ የክ/ከተማው ፀጥታ አስተማማኝ የሆነበት የወንጀል ምጣኔን መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል። 

ኃላፊው አክለውም ከፊት ለፊታችን የሚመጡ የአደባባይ ኩነቶች መኖራቸውን ጠቁመው ጥምር የፀጥታ ሀይሉ የእስካሁኑን የሰላም ማስከበር ስራውን አጠናክሮ በማስቀጠል የከተማችንን ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል። ከተማችን ላይ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ሰላምን ለማደፍረስ  የሚተጉ ፀረ ሰላም ግለሰቦችና ቡድኖችን እንቅስቃሴ የፀጥታ ጥምር ሀይሉ በቅንጅትና በመናቡብ መስራት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው አሳስበዋል።

ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ የልደታ ክ/ከተማ  ዋና ስራ አስፈፃሚ  እንዳሉት በመንግስት መዋቅር መደበኛ ስራዎች ያለምንም የፀጥታ ሰጋት እንደሚከናወንና ህብረተሰባችን ያለፀጥታ ስጋት እንዲከናወን የሰላም ማስጠበቅ ስራውን እየሰሩ ለሚገኙ የፀጥታ ጥምር ሀይሎች ምስጋናን አቅርበዋል።

ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም ኢትዮጲያን ወደፊት የሚያሻግር ሀሳብ የተነሳበት ሀገር የመከረችበት ወቅት እንደመሆኑ የሀገርና የከተማን ሰላም ማፅናት እንደሚያስፈልግ ገልፀው  የፀጥታ ጥምር ሀይሉ የአካባቢን ሰላም በንቃት በመጠበቅ ሰላሟ የተረጋገጠባት ከተማነቷን ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ነሀሴ 21/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157