የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በወቅቱ መፍታትና...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በወቅቱ መፍታትና የሕዝብ ቅሬታን መቀነስ ለፀጥታ ሥራ መሳካት ከፍተኛ አበርክቶ አለው።

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በወቅቱ መፍታትና የሕዝብ ቅሬታን መቀነስ ለፀጥታ ሥራ መሳካት ከፍተኛ አበርክቶ አለው።

አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አማካሪ 

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ  አፈታት ሂደትን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመገምገም  የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ልየታ መድረክ ከሁሉም ክ/ከተማ የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

 አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አማካሪ እንዳሉት ባለፈው በጀት ዓመት የከተማውን ሰላምና ደህንነትን ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ  ስራዎች እንደተሰሩ ገልፀው   የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በወቅቱ መፍታትና የሕዝብ ቅሬታን መቀነስ ለፀጥታ ሥራ መሳካት ከፍተኛ አበርክቶ አለው ብለዋል።ቢሮው  ቅሬታዎችን በመቀነስ ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ማስቻል ተችሏል ያሉት አማካሪው  ከህብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን  መፍታት ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትስስር  መስራት የዜጎችን በሰላም ወጥቶ  መግባት እንዲሁም ደህንነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስችልና  የሚሰጡ አገልግሎቶችም በተዋረድ ቅሬታዎችን ለመፍታት እንደሚያስችል ገልጸዋል።

አማካሪው አያይዘውም ህብረተሰቡን በማወያየት በመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ልየታ በማድረግና ወደ ዕቅድ በመቀየር መስራትም እንደተቻለ ገልጸው ህዝቡን በአገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት በታማኝነት በማገልገል ፈጣን ምላሽ ስርአት በመዘርጋት   እየተሰራ ነው ብለው ይህን ውጤታማ ለማድረግ  የጋራ የቅንጅት ስራ እንደሚጠይቅና ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ወ/ሮ አለም ጸሀይ ማሞ የቢሮው የስታንዳርዳይዜሽንና የአገልግሎት አሰጣጥ ምዘናና ክትትል ድጋፍ ዳይሬክቶሬት   የ2018 በጀት ዓመትን አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመትን ዕቅድ ያቀረቡት  ሲሆኑ የተሰሩ ስራዎችንና በቀጣይ ስለሚሰሩ ስራዎች ሲያብራሩ የጋራ መግባባት በመፍጠር ከተጠያቂነት ፣ ፈጣን ምላሽ ከመስጠት፣ ከቅልጥፍና ፣ የስጋት ቀጠናዎችን የመለየት፣ በጫኝና አውራጁ መመሪያ አተገባበር ላይ፣ የህብረተሰቡን ቅሬታ መፍታት ፣ በየት/ቤቶች አካባቢ የሚፈጠሩ የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያዉኩ ድርጊቶች ላይ እርምጃ ማስወሰድ ፣ የኢኮኖሚ አሻጥር የሚፈጥሩ ነጋዴዎችን እርምጃ የማስወሰድ የመንገድ መብራቶች እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ምቹ እንዲሆኑ የማድረግ ስራዎች ሲሆኑ በቀጣይ የተሻለ በመስራት የከተማው ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ እንደሚገባ በዕቅድ ሪፖርቱ ተመልክቷል።

ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው በመልካም አስተዳርና አቤቱታ አፈታት ላይ በጋራ በመስራት  ከሰላም ጎን በመቆም ተልዕኮን በመቀበል ወደ ተሻለ ሀገር ተርታ እንድትሰለፍ በማድረግ የበኩላቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡ ገልጸዋል።

ነሀሴ 21/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157