የህዝብ ለህዝብ ትስስርን በማጠናከር ፤ የሀገርን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የህዝብ ለህዝብ ትስስርን በማጠናከር ፤ የሀገርን ቅርስ በመጠበቅ ነገን አሻግሮ የሚያይ ትውልድ በመገንባት ላይ የሀይማኖት ተቋማት ትልቁን ሚና እየተወጡ ይገኛሉ።

የህዝብ ለህዝብ ትስስርን በማጠናከር ፤ የሀገርን ቅርስ በመጠበቅ ነገን አሻግሮ የሚያይ ትውልድ በመገንባት ላይ የሀይማኖት ተቋማት ትልቁን ሚና እየተወጡ ይገኛሉ።

አቶ ብርሀኑ ረታ  የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ 

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ከአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን  ሰው ተኮርና ነበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ያደረጉትን አስተዋጽኦ ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት እንዲሁም የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሰራርና አደረጃጀት ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል።

አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ  እንዳሉት  የመጣንበትን በመፈተሽ የትናንት ውጤትን በመሰነቅ አካሄድን በማስተካከል   በርካታ ስራዎችን እየተሰሩ መሆናቸውን አንስተው  ቢሮው  በሀገር ግንባታ ላይ ከሁሉም ቤተ እምነቶችና አባቶች ጋር በዋነኝነት የሰው ልብና አዕምሮ ላይ በመንፈስ በአካል አንድ የሆነ ማህበረሰብ ለመፍጠርና የማይናወጥ ሀገር መገንባትም ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ትውልድን በመገንባት ሂደት ላይ የየቤተ እምነቱ አባቶች በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው  የገለፁት  የዘርፉ ኃላፊ የህዝብ ትስስር መሳሪያ የሀገር ቅርስ መጠበቅ ማለት ነገን አሻግረን የምናይበት ሀገርን በፅኑ መሰረት ማቆም ነው ለዚህም  የሀይማኖት ተቋማት ትልቁን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

አቶ ብርሀኑ አያይዘውም ቢሮው ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በከተማው ላይ በሚሰራው ስራ ላይ ውጤታማ መሆኑን አስታውሰው በአለም መድረክ ላይም እንደ ሀገር ሽልማትን ማግኝት ችለናልም ሲሉ  ለጸጥታ ስራ የሁሉም ማህበረሰብን ትጋት የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እሱን በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባልም ሲሉ አቶ ብርሀኑ ተደምጠዋል።

ሼህ አብዱል ሀሚድ አህመድ  የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ም/ዋና ጸሀፊ በመድረኩ በመገኝት እንዳሉት ያለፈውን ጊዜ ሁሉ  በበለጠ ሰርተን በሰላምና ማህበራዊ ስራዎች ላይ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩና እየተሰሩም እንደሆነ ገልፀው አብሮነትን በማጠናከር በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲውሉ በስነ ምግባር የታነጸ ማህበረሰብ መፍጠር ላይ የሚሰሩትን ስራ አጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የሀይማኖት አባቱ አክለውም  በቀጣይም በከተማው ላይ ለሚከናወን ማንኛውም አስተዋጽኦ ላይ በመሳተፍ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡና የሀገርን አንድነት በጽኑ መሰረት ላይ እንድትቆም ሁሉም በየቤተ እምነቱ አስተምህሮቱን በማጠናከር በጸሎት  ሀገራቸውን እንዲያስቡ አሳስበዋል።

በወጣት ዩሀንስ ግርማ ከአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በመጡ ባለሙያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሰራር አደረጃጀት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናውም  ስለሰላምና አብሮነት፣ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ የቆዩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች ዙሪያ ያተኮረ ነው።

አቶ ታጠቅ ነጋሽ  የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በሰው ተኮርና የበጎ ፈቃድ ስራዎች ግምገማና የ2019 ዕቅድ ላይ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ በደም ልገሳ፣በቤት እድሳት ሌሎችም ስራዎች እንደተሰሩ አብራርተው በቀጣይም ስለሚሰሩ ስራዎች ላይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው በመልካም አስተዳደር ብልሹ  አሰራር ላይ የሚነሱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ቢደረግ፣በየ ቤተ እምነቱ ያሉ ችግሮችን በማረም ተጠናክረው እንደሚሰሩ በጎ ተግባር ላይ በመሳተፍ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ከተሳታፊዎቹ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ከመድረኩ ምላሽ ተሰቶበታል።

በመድረኩ ላይ አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ፣ሼህ አብዱል ሀሚድ አህመድ  የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ም/ዋና ጸሀፊ፣የሁሉም ቤተ እምነት አባቶች፣የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የወረዳና የክ/ከተማ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።

ነሀሴ 21/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157