የአካባቢያችን እና የማህበረሰቡ ሰላም የኛም ሰላም ነው!" የሰላም ሰራዊት አባላት
"የአካባቢያችን እና የማህበረሰቡ ሰላም የኛም ሰላም ነው!"
የሰላም ሰራዊት አባላት
ነሀሴ 15/2018 ዓ.ም
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አሰተዳደር የአንድ ማዕከል የሰላም ሰራዊት የፀጥታ ስምሪት ተሰጠ ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው እና የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዲስ ዘውዴ በስምሪቱ ላይ ተገኝተዉ ስምሪት ሰጥተዋል።
በስምሪቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው የሰላም ሰራዊቱ ማህበረሰቡን በማንቀሳቀስ ረገድ ያለዉ ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ ከተማ አቀፍ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ ህዝባዊ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት በመስጠት ገልፀዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አዲስ ዘውዴ ባስተላለፉት መልዕክት ለሰላም ሰራዊት አደረጃጀቱ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀው፤ የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ ኃላፊነት በመውሰድ እየሠሩ በመሆናቸው አድናቆታቸውን ገልፀዋል። ይህንን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉና ከአስተዳደሩ እና ከፀጥታ አካላት በሁሉም ዘርፍ እየሰሩ ያሉትን ተግባራት አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም አዋኪ ድርጊቶችና ስርቆት ሌሎች ወንጀሎች ሲፈጸሙ ሠላም ሠራዊቱ እና ነዋሪው በአከባቢው ላለ የጸጥታ አካላት በመንገር ወንጀል በጋራ መከላከል እንደሚገባ ገልጸዋል።