ማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል...

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ህዝቡን የሰላም ባለቤት የማድረግ ተግባርን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።

ማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ህዝቡን የሰላም ባለቤት የማድረግ ተግባርን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።
    
      አቶ ፍስሐ ጥበብ 
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2019  በጀት አመት ዕቅድ ላይ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ከሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱን የመሩት አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ እንዳሉት የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምን በማጎልበት ስራን በተሰጠው ልክ ቆጥሮ በማከናወን በማስረከብ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ማዕከል ያደረጉ ስራዎችን በማከናወን ህዝቡ የሚያነሳቸውን  ጥያቂዎች  መፍታትና የነዋሪውን ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በውይይት የሚያምን ማህበረሰብ በመገንባት የነዋሪውን አመለካከት   በጸጥታ አጠባበቅ ስራ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን  በመቅረጽ  ፣ ማህበረሰብ አቀፍ  ውይይቶችን በማጠናከር ፣ አካባቢያቸውን ከጸጉረ ልውጥ ከሽብር ሀይሎች ከወንጀለኞች እንዲጠብቁና እንዲያጋልጡ ነዋሪውን ግንዛቤ በመፍጠር ከጸጥታ አጋዥ ሀይሎችና ከቅጥር ጥበቃዎች ጋር  አብሮ በመስራት የከተማው ሰላም በዘላቂነት ማስቀጠል ይጠበቅብናል ሲሉ አቶ ፍስሐ ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

የዘርፉን የ2019 በጀት አመት ዕቅድ ላይ  ገለጻ ያደረጉት የዘርፉ ዳይሬክቶሬት  አቶ አብርሃም እንግዳወርቅ በዋነኝነት ዕቅዱን ሲያብራሩ የሰላም ሰራዊቱን አደረጃጀት ማጠናከር ፣ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት የማድረግ ፣ ህዝቡን ያሳተፈ የሰላም የጸጥታና የደህንነት ስራዎች ማከናወን ፣ አካባቢዎችን ከወንጀለኞች ነጻ የማድረግ ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ መረጃ ማደራጀት የተቋምን ግንባታና የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነትን ማሳደግ ፣ የመልካም አስተዳደር  ችግሮችን በመፍታት ቅሬታን የመቀነስ አሰራር መዘርጋት በዋናነት የዕቅዱ አካል መሆናቸውን አብራርተዋል።

ባለሙያዎቹ በበኩላቸው ከባለፈው ዓመት በይበልጥ ተጠናክሮ ስራዎችን በማከናወን ዘርፍ አሁን ላይ ከህብረተሰቡ ጋር እየሰራበት ያለውን አግባብነት በማጠናከር  በተጀመረው በጀት ዓመት ለበለጠ ውጤታማነት እንደሚሰሩ ገልፀው ከባለፈው ዓመት ላይ የጋጠሙ ችግሮች እንዲፈቱ አንስተዋል።  

በመጨረሻም ዘርፍ በ2019 በጀት አመት ዕቅድ ላይ በመወያየት ከሁለቱም የዘርፉ ዳይሬክተሮችና  ከአስራ አንዱም ክ/ከተማ የዘርፉ አስተባባሪዎች ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የፊርማ ስነስርዓት አከናውነዋል።

ነሀሴ 15/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157