የጋራ ውይይት ለውጤታማ ሥራ ወሳኝ ነው።
የጋራ ውይይት ለውጤታማ ሥራ ወሳኝ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ የዘርፉ ዳይሬክቶሬቶች ፣ አስተባባሪዎችና ሙያተኞች ጋር ውይይት በማድረግ በዕቅዱ ላይ የስምምነት ፊርማ አካሄደ።
በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ባደረጉበት ወቅት፣ውጤታማና የተቀናጀ ሥራን ለማስመዝገብ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ አካላት በጋራ መወያየትና የሥራ ዕቅዳቸውን በአንድ አቅጣጫ ለማስኬድ የጋራ ውይይቱ የሥራ አቅጣጫዎችን ለማጠናከር እና የተግባር ቅንጅትን ለማሳደግ የሚጠበቁ ውጤቶችን በተገቢው ማስመዝገብ ወሳኝ መሆኑም ተገልጿል።
የተቋማት ቅንጅት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና ፈጣን ምላሽ የወንጀል መከላከል ሥራን ውጤታማ ያደርጋሉ ያሉት ኃላፊው የውይይቱ ዋና ዓላማ ዕቅድን ካስኬድ በማድረግ የጋራ መግባባት በመፍጠር ለጋራ ውጤታማነት በቅንጅት በመስራት የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
በመድረኩ የበጀት ዓመቱ የፀጥታ ኦፕሬሽን ተግባራት፣ የሥራ ቅድሚያዎች፣በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራትና የሚጠበቁ ውጤቶች በዝርዝር የቀረበ ሲሆን፣በተጨማሪም የዕቅዱን አፈጻጸም ለማጠናከር በማዕከል፣ በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ ያሉ አካላት በቅንጅትና በተጠያቂነት እንዲሰሩ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ የማህበረሰብ አቀፍ የፀጥታ አጠባበቅ እና የተቋማት ደህንነት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳምጠው አያሌው በዕቅዱ አብራርተዋል።
ተሳታፊዎችም በዕቅዱ ዙሪያ ያላቸውን ሀሳብና የሥራ ልምድ በማካፈል፣ በአፈጻጸም ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችንና መፍትሔዎችን በመጠቆም በዕቅዱ ላይ ገንቢ ውይይት አድርገዋል።
በመጨረሻም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱ ከማዕከል እስከ ወረዳ ባሉ የፀጥታ ኦፕሬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የጋራ ዕቅድ እንዲሆን በማድረግ፣ የተቀናጀ አፈጻጸምን በማረጋገጥ ለከተማዋ ሰላምና ፀጥታ የበለጠ ውጤታማ ሥራ ለማከናወን ተሳታፊዎች ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።
የ2019 በጀት ዓመት የሥራ ስምምነት ሰነድ ከ11ዱም ክ/ከተሞች ከዘርፉ አስተባባሪዎች ጋር ተፈራርመው፣የሥራ ስምምነቱ በበጀት ዓመቱ የሚከናወኑ የሥራ አቅጣጫዎችን፣ተግባራትንና የሚጠበቁ ውጤቶችን በጋራ በመወሰን በተቀናጀና በተጠያቂነት የተመራ አፈጻጸም ለማረጋገጥ መሠረት የሚጥል ሲሆን፣ የሁሉም ክ/ከተሞች ተሳትፎና ትብብር የታቀዱ የፀጥታና የህግ ማስከበር ተግባራትን በተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል።
ነሀሴ 15/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157