ትናንትን በታሪክ ውስጥ በማለፍ ዛሬን ለኢትዮጵያ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ትናንትን በታሪክ ውስጥ በማለፍ ዛሬን ለኢትዮጵያውያን የማይሻር ህልውና በማሻገር ለትውልድ የሚጠቅም ሀገር በመገንባት ሂደት ውስጥ ሴቶች የማይተካ ሚና እየተወጡ ይገኛሉ።

ትናንትን በታሪክ ውስጥ በማለፍ ዛሬን ለኢትዮጵያውያን የማይሻር ህልውና በማሻገር ለትውልድ የሚጠቅም ሀገር በመገንባት ሂደት ውስጥ ሴቶች የማይተካ ሚና እየተወጡ ይገኛሉ።

   አቶ ብርሀኑ ረታ 
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ 

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሴቶች ለሀገር ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ያላቸው ሚና በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ "የሰላም ባለቤትነት ለሴቶች፤ለሰላማዊና ጤናማ ማህበረሰብ ግንባታ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከክ/ከተሞች ለተውጣጡ ሴቶች  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰቷል።

በስልጠናው ላይ በመገኝበት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ሲሆኑ በሀገር አቀፍና በከተማ ደረጃ ሴቶችን በማሳተፍ በሀገር ግንባታ ላይ መግባባትን በመፍጠር ሴቶች ያላቸው ሚና የጎላ እንደሆነ በመግለፅ ሴቶች የአብሮነት እህትማማችነት አንድነት በመፍጠር በኩልም ሚናቸው አይተኬ መሆኑን ገልፀዋል።

ሀገር በሴቶች እንደምትመሰል ሁሉ በከተማችን አዲስ አበባ ላይ ባለፍት የለውጥ አመታት ውስጥ የሴቶች ሚና እንዲጎለብት በማድረግ ትላልቅ ተቋማትንም  በመምራት ሰርተው በማሳየትና በማስመስከር ደረጃ የመቻል ምሳሌም እንደሆኑ አብራርተው ትላንት በታሪክ ውስጥ በሰሩት ስራ የምንኮራ በነጻነት ቀንዲል ውስጥ ያለሴቶችም ተሳትፎ እንዳልጸና ሁሉ ዛሬም ትላልቅ አሻራን እያስቀመጡ ይገኛሉም በማለት ሴቶች የማድረግ የመቻል የፍጻሜ ማሳያ በመሆን በሀገር ግንባታ ላይም ሚናቸው የጎላ መሆኑን ሀላፊው ገልጸዋል።

ሀላፊው አያይዘውም ሀገራዊ ተልእኮ ላይ በመስራት በመተባበር የተሻለ ሀገርና ከተማ በማስረከብ ላይ ሴቶች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንደመሆናቸው  በይቅር ባይነትና በፍቅር ተሻጋሪ ትውልድን በመፍጠርና ሀገር በመገንባት ትውልድ የመቅረጽ ስራ የመስራት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ  አሳስበዋል።

ሰላም የሁሉም ዋልታና መሰረት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የአካባቢ ሰላም እንዲሰፍን አስተማማኝ ሰላም በከተማው ላይ እንዲረጋገጥ በማድረግ በፖለቲካ በማህበራዊ ጉዳይ ላይ በመሳተፍ ፤  የሀገርን ዕድገት የማይፈልጉ አካላት ሌት ተቀን ሰላም ለማደፍረስ ስለሚጥሩ የጠላት ሀይሎችን ሴራ የማክሸፍ ፣ ጸጉረ ልውጥ እንቅስቃሴዎች በመቆጣጠር ወንጀልን በመከላከል በኩል ሁሉም ማህበረሰብ በይበልጥ ደግሞ ሴቶች ግንባር ቀደም በመሆን የሰላም ዘብ እንዲሆኑ አደራ እላለሁ ሲሉ ኃላፊው ተደምጠዋል ።

ስልጠናው የሰጡት አቶ ሙሉቀን እንየው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖትና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት ሀገር ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ላይ ስለመሳተፍ ፣ ግብርና ንግድ የሀብት አሰተዳደር ፖለቲካ ሚና ተሳትፎና አመራርነት ላይ ግጭት መከላከልና አፈታት፣ባህል ሽግግር አስተላላፊነት ላይ፣የቤተሰብ አስተዳደርና የሀገር ኢኮኖሚ ላይ፣ስለ ኢኮኖሚያዊና የቁጠባና የስራ ባህል በፖለቲካ መድረክ ስለመሳተፍ፣ስለመልካም አስተዳደር የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ይገኙበታል ።

ሰልጣኞቹ በበኩላቸው ያገኙትን ዕውቀት ለሌሎች በማጋራት ተግባራዊ እንደሚያደርጉና ከምን ጊዜውም በበለጠ የተለዩ አለ መግባባቶች በውይይት በመፍታት ለሰላም የጀርባ አጥንት በመሆን እንደሚሰሩ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

ነሀሴ 15/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157