ለከተማችን ሰላምና ፀጥታ በቅንጅት፣ በንቃትና በሕግ አክብሮት እንስራለን።
ለከተማችን ሰላምና ፀጥታ በቅንጅት፣ በንቃትና በሕግ አክብሮት እንስራለን።
የጉለሌ ክ/ከተማ ሰላም ሰራዊት በአንድ ማዕከል ስምሪት ላይ የተናገሩት
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በጉለሌ ክ/ከተማ የአንድ ማዕከል የፀጥታ የሰላም ሰራዊት ስምሪት የሰጠ ሲሆን ቢሮው ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የከተማዋን ዘላቂ ሰላም እያረጋገጠ ነዋሪው ያለምንም የፀጥታ ስጋት ወጥቶ መግባት እንዲችል በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በስምሪቱ ላይ ተገኝተው እንዳሉት ኢትዮጲያ እንደ ጥበብ በህብረቀለም ያሸበረቀች ፣ በብዝሀነት የተዋበች ሀገር እንደመሆኗ ከጥበቡ አንድም ክር እንዳይቀነስ እርስ በርስ በመከባበርና በመተሳሰብ አንድም ማንነት እንዳይጎድል መስራትና የአካባቢን ሰላም በመጠበቅ የፅንፈኞችን ሴራ ማክሸፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የሰላም ሰራዊት የሰላም ዘብ በመሆን ለሰላማዊ ከተማ መተባበር ይገባል ያሉት ዘርፍ ኃላፊው የአካባቢን ሰላም በመጠበቅና የከተማን ሰላም በማረጋገጥ ከመደበኛ የፀጥታ አካሉ ጋር በመሆን በቅንጅት መስራትና የመረጃ ምንጭ ላይ በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል።
አቶ ወልዴ ወገሴ የጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ከተማችን ሰላሟ የተረጋገጠባት ከተማ እንድትሆን የከተማችን ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት የሚሰራው ስራ የሚመሰገን መሆኑን ጠቁመው በተለይም ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የአካባቢን ሰላም በማሰጠበቅ የከተማዋን ሰላም የማረጋገጥ ስራ ውጤታማ እንደሆነ ገልፀዋል።
ስራ አስፈፃሚው አክለውም እንደ ጉለሌ የተደራጀው የሰላም ሰራዊት የአካባቢን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ፣ ከመደበኛ የፀጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት በጋራ የፀጥታና የወንጀል ጥቆማዎችን በመስጠት የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ ነዋሪው ያለምንም የፀጥታ ስጋት መንቀሳቀስ እንዲችል አስችለዋል ብለዋል።
በስምሪቱ ላይ የቢሮው ምክትል ኃላፊዎች አቶ ፍስሀ ጥበቡና አቶ ብርሀኑ ረታ እንዲሁም የክ/ከተማው ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ አመራሮች ተገኝተዋል።
ነሀሴ 14/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157