ትክክለኛ መረጃ፣ ፈጣን ምላሽ፣ ዘላቂ ሰላም!”
“ትክክለኛ መረጃ፣ ፈጣን ምላሽ፣ ዘላቂ ሰላም!”
የፀጥታ መረጃን በወቅቱ መሰብሰብ፣ ማጣራትና ማስተላለፍ ለከተማችን ሰላምና ፀጥታ መረጋገጥ ወሳኝ ነው።
ዶ/ር ወንድማገኝ ታደሰ
(የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ኃላፊ )
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ መረጃ ዘርፍ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት በማድረግ የስምምነት ሰነድ የፊርማ መርሐግብር አካሄደ።
ዶ/ር ወንድማገኝ ታደሰ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ኃላፊ በመድረኩ ላይም የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን በማቀናጀትና ጂአይኤስን (GIS) ጨምሮ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የፀጥታ ስጋት ያላቸውን ቀጠናዎች በካርታ ላይ በመለየት፣መረጃዎችን መሰብሰብ፣ መመደብና መተንተን በማስቻል ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት በመለየት የቅድመ መከላከልና የህግ ማስከበር ስራዎችን በመረጃ ላይ በመመስረት በማጠናከር መስራት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።
ኃላፊው አክለውም የፀጥታ መረጃን በወቅቱ መሰብሰብ፣ ማጣራትና ማስተላለፍ ለከተማችን ሰላምና ፀጥታ ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ማንኛውም የከተማው ነዋሪ አጠራጣሪ መረጃን ሲመለከት በኃላፊነት በማሳወቅ የሰላም ዘብ መሆን ይጠበቃል ብለዋል።
ወ/ት ዳግማዊት ቸርነት የፀጥታና መረጃ ዘርፍ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመድረኩ እንዳሉት የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን፣በገለጻቸውም እንዳሉት የፀጥታ መረጃ ዘርፍ የሚያከናውናቸው ዋና ዋና የሥራ አቅጣጫዎች፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራትና የሚጠበቁ ውጤቶች በዕቅዱ በዝርዝር አቅርበዋል።
የፀጥታ መረጃ ሥራ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ፣ ሊከሰቱ የሚችሉ የፀጥታ ስጋቶችን አስቀድሞ ለመለየትና በወቅቱ ምላሽ ለመስጠት ወሳኝ መሆኑ በመድረኩ ተጠቁሞ፣በዚህም የመረጃ አሰባሰብና ትንተና አቅምን ማጎልበት፣ በተለያዩ የፀጥታ አካላት መካከል የመረጃ ቅንጅትን ማሳደግ፣ የሚገኙ መረጃዎችን በወቅቱና በተገቢው መንገድ በመተንተን ለውሳኔ ሰጪዎች ማቅረብ እንዲሁም የመረጃ ሥራን በቴክኖሎጂ ማጠናከር እንደ ዋና የሥራ አቅጣጫዎች ዳይሬክተሯ አንስተዋል።
አክለውም፣የፀጥታ መረጃ ዘርፍ የነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳን በማካሄድ ቀጠናዊ የፀጥታ ፈተናዎችንና ወቅታዊ ክስተቶችን፣የፀጥታ ስጋት ቦታዎችን በመለየት ከፀጥታ ኦፕሬሽን ጋር በቅንጅት የቅድመ መከላከልና ቁጥጥር ሥራ እንዲሁም እርምጃ የመውሰድ ስራ አጠናክሮ የሚሠራ መሆኑም በዕቅዱ ገልጿል።
በመድረኩ ተሳታፊዎች በዕቅዱ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችና ግብዓቶችን በማቅረብ ዕቅዱ በተግባር የሚፈጸምና የሚጠበቀውን ውጤት የሚያስገኝ እንዲሆነ አንስተው፣
የ2019 በጀት ዓመት የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ዕቅድ በተቀናጀ፣ በተጠያቂነትና በውጤት ተኮር አሠራር በመፈጸም ለከተማዋ ሰላምና ፀጥታ ዘላቂነት የራሱን የላቀ አስተዋፅዖ ለማበርከት ቁርጠኝነት ተገልጿል።
በመጨረሻም የ2019 በጀት ዓመት የሥራ ስምምነት ሰነድ ከ11ዱም ክ/ከተሞች ከዘርፉ አስተባባሪዎች ጋር ተፈራርመው፣የሥራ ስምምነቱ በበጀት ዓመቱ የሚከናወኑ የሥራ አቅጣጫዎችን፣ተግባራትንና የሚጠበቁ ውጤቶችን በጋራ በመወሰን በተቀናጀና በተጠያቂነት የተመራ አፈጻጸም ለማረጋገጥ መሠረት የሚጥል ሲሆን፣ የሁሉም ክ/ከተሞች ተሳትፎና ትብብር የታቀዱ የፀጥታና የህግ ማስከበር ተግባራትን በተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል።
ነሀሴ 14/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157