ቢሮው ሲያሰለጥን የነበረውን አጋዥ የፀጥታ ሀይሎ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮው ሲያሰለጥን የነበረውን አጋዥ የፀጥታ ሀይሎችን አስመርቆ ወደ ስራ አስገባ።

ቢሮው ሲያሰለጥን የነበረውን አጋዥ የፀጥታ ሀይሎችን አስመርቆ ወደ ስራ አስገባ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ  ባለፉት አምስት አመታት ከህብረተሰቡ የተውጣጡ በጎ ፈቃደኛ ነዋሪዎችን በሰላም ሰራዊት በማደራጀት የአካባቢን ብሎም  የከተማን ሰላም የማስጠበቅ ስራ እየሰራ ይገኛል።

 ከሰላም ሰራዊቱ  በተለያየ ምክንያት የተጓደሉ  አባላት ለመተካት  ባሳለፍነው ሳምንት በ11 ዱም ክ/ከተሞች በንድፈ ሀሳብና በመስክ ወታደራዊ ስልጠና ሲያሰለጥን የቆየውን ዛሬ በሁሉም ክ/ከተሞች አስመርቆ ወደ ስራ አስገብቷል።

የሰላም ሠራዊቶች  ሰላምን  የሚያስከብሩ፣ ግጭትን በውይይት የሚፈቱ፣ ለህብረተሰቡ አርአያ የሚሆኑ በጎ ፈቃደኛ ዜጎች እንደመሆናቸው ለሰላም መቆም ፣ ለአንድነት መስራት፣ ልዩነቶችን በመከባበር መፍታት እና  ከመደበኛ የፀጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው  አቅጣጫ ተሰጥቷል ።

በምረቃ ምርሐግብሩ ላይም የቢሮው ከፍተኛ የስራ  ኃላፊዎች የክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች የተገኙ ሲሆን ለሰልጣኞቹ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

ነሀሴ 14/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157