ባለፋት አምስት አመታት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ፤ የሰላም ሰራዊቱን የሰላም ዘብ በማድረግ ወንጀሎች እንዲቀንሱ የማድረግ ስራዎች ተሰርተዋል።
ባለፋት አምስት አመታት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ፤ የሰላም ሰራዊቱን የሰላም ዘብ በማድረግ ወንጀሎች እንዲቀንሱ የማድረግ ስራዎች ተሰርተዋል።
አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ
ሀላፊው ይህንን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በ2018 በጀት አመት በተጓደሉ የሰላም ሰራዊት አባላት ማሟያ በንድፈ ሀሳብና ወታደራዊ የመስክ ስልጠና የተግባር ማነቃቂያ ስልጠና በሁሉም ክ/ከተሞች ሲሰጥ ቆይቶ በዛሬው ዕለት የማጠቃለያ መርሐ ግብረ ላይ ነው ።
በአራዳ ክ/ከተማ ማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፍት አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ሲሆኑ ባለፋት አምስት አመታት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት የሰላም ሰራዊቱን የሰላም ዘብ በማድረግ ወንጀሎች እንዲቀንሱ የማድረግ ስራዎች ተሰርተዋል በማለት በከተማው ላይ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖርም በማድረግ ነዋሪው በሰላም ወጥቶ እንዲገባ የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ ማድረግም እንደተቻለ ገልፀዋል።
የከተማውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ህብረተሰቡ በየደረጃው ሰላምን የግሉ አድርጎ መጠበቅ አንዱና ዋነኛ ተግባር ሊሆን ይገባልም ያሉት ሀላፊው በቅንጅትና በጋራ ሲሰራ የከተማውን ሰላም አስተማማኝ ማድረግም የአንድ አካል ብቻ ባለመሆኑ በቅንጅት በመሰራት አሁን ላይ ላለበት ሰላም ወሳኝ ሚና እንዳለውም አብራርተዋል።
አቶ ፍስሐ አያይዘውም የሰላም ሰራዊቱ በየአካባቢው ለሚኖረው የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳትፎአቸውን በማጠናከር ግጭቶችን በመፍታት ጸጉረ ልውጥ እንቅስቃሴዎች በመለየት መረጃን ለሚመለከተው አካል በማቀበል ወንጀለኛን በማጋለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦም እየተወጡ እንደሚገኙ ገልፀው ማህበረሰቡ ወጥ የሆነ የጸጥታ አጠባበቅ ግንዛቤ እንዲኖረውም ማድረጉን ገልፀዋል
አቶ ወንድሙ ዑመር የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በመርሐግብሩ ላይ ተገኝተው እንዳሉት የሰላም ሰራዊቱ ከህብረተሰቡ ጋር በመናበብና በመግባባት እየሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ ነው ብለው በዚህም በክ/ከተማው ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር በማድረግ ስርቆት ንጥቂያዎችና መሰል ወንጀሎችን መቀነስ ችለዋል ብለዋል። አክለውም ዛሬ ወደ አባላቱ የተቀላቀሉ ሰልጣኞች ይህን ተግባር በይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።
በመጨረሻም በስልጠናው ለተሳተፉት የጸጥታ አካላት የማበረታቻ የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸው የሰላም ሰራዊቶቹ ሀገራቸውንና ህብረተሰቡ በፍትሀዊነት እንዲያገለግሉ ቃል ገብተዋል።
ነሀሴ 14/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157