የሰላም ሰራዊቱ ከነዋሪውና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሁሌም የአካባቢውን ሰላም በንቃት በመጠበቅ እያደረገው ያለው ተሳትፎ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል"!!
"የሰላም ሰራዊቱ ከነዋሪውና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሁሌም የአካባቢውን ሰላም በንቃት በመጠበቅ እያደረገው ያለው ተሳትፎ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል"!!
አቶ ፍስሃ ጥበቡ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ
ነሀሴ12/2018 ዓ.ም
የሰላም ሠራዊት አባላት የአካባቢ ሰላምን በማስጠበቅና ቅድመ ወንጀልን በመከላከል ጉልህ ሚና እየተወጡ መሆኑ ተገለፀ
በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአንድ ማዕከል የሰላም ሠራዊትና የፀጥታ መዋቅር ስምሪት የከተማና የክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በወረዳ 06 በሚገኘው 28 ሜዳ ላይ ተሰጥቷል።
ስምሪቱ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በማስጠበቅ፣ ቅድመ ወንጀልን በመከላከልና የህብረተሰቡን ደህንነት በማረጋገጥ የተሻለ የሰላም ሁኔታ መፍጠር መሆኑ ተገልጿል።
በአንድ ማዕከል ስምሪት አሰጣጡ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍስሐ ጥበቡ እንደገለፁት የሰላምና ፀጥታ ሥራ የተወሰነ ጊዜና ቦታ የማይገድበው በመሆኑ በቅንጅትና በተቀናጀ መልኩ መሥራት የአካባቢውንና የከተማዋን ሰላም ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
አቶ ፍስሐ አክለውም አሁን ያለንበት ወቅት ከፀጥታ አንፃር ልዩ ትኩረትን የሚጠይቅ በመሆኑ የአካባቢውን ፀጥታ በትጋት 24/7 መጠበቅ እንደሚገባ በማሳሰብ በተለይም የሰላም ሠራዊት አባላት በቅድመ ወንጀል መከላከልና የህብረተሰቡን ሰላም በማስጠበቅ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ በበኩላቸው የሰላም ሠራዊት አባላት ከመደበኛው የፀጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀትና በተቀናጀ አሠራር በመስራት አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያደርጉት ሚና የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።
የሰላምና ደህንነት ሥራውም ከተለመደው መዋቅራዊ አሠራር በተጨማሪ ህብረተሰቡን በማሳተፍና የሰላም ሠራዊትን ሚና በማጠናከር በቀጣይነት እንደሚጠናከር አቶ ሀብታሙ ገልጸዋል።
የሰላም ሠራዊትና የፀጥታ መዋቅሮች በቅንጅት በመሥራት ቅድመ ወንጀልን በመከላከል፣ የህብረተሰቡን የሰላም ንቃተ ህሊና በማጎልበትና የአካባቢውን ፀጥታ በማስጠበቅ የየካ ክፍለ ከተማን ሰላም ለማረጋገጥ የሚያደርጉት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157