ወጣቶች በከተማዋ ሰላምና ፀጥታ ላይ የሚኖራቸው ሚና እንዲጎለብት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
ወጣቶች በከተማዋ ሰላምና ፀጥታ ላይ የሚኖራቸው ሚና እንዲጎለብት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከከተማዋ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር “የጋራ መግባባትና ስምምነት ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ቃል የጋራ የንቅናቄ መድረክ ለማካሄድ የሚያስችል መነሻ ዕቅድን ተወያይተው አፀደቁ።
በመድረኩ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ በማስጠበቅ ዙሪያ የወጣቶችን ሚና ማጠናከር፣ በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ የወጣቶችን ግንዛቤ ማሳደግ እንዲሁም ወጣቶች ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በቅንጅት እንዲሠሩ ምቹ ሁኔታ መፍጠር በዋናነት ተነስቷል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት ወጣቶች በሀገራዊና ከተማ አቀፍ አጀንዳዎች ላይ ተሳታፊ ማድረግ በመቻሉ ምክንያታዊ ወጣት መፍጠር ተችሏል ብለዋል።
ወጣቶች በሰላምና ፀጥታ ሥራዎች ያላቸው ተሳትፎ እንዲጎለብት ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ቢሮ ኃላፊዋ ግጭትን በሰላማዊ መንገድ መፍታትን ባህል እንዲያደርጉ ፣ የአካባቢያቸው ሰላም በመጠበቅ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ እና ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በተቀናጀ መልኩ እንዲሠሩ ማስቻል ብሎም የጋራ ሰላምን ለማረጋገጥ ተሳትፎአቸውን ለማሳደግ ያለመ የንቅናቄ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል።
በተለይም የከተማዋን ህብረ ብሔራዊ አንድነት የሚያጠናክሩ የሃይማኖት፣ የሕዝብና የአደባባይ በዓላት በፍጹም ሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበሩ፣ ወጣቶች እንግዶችን በመቀበልና ሰላምን በማስጠበቅ የሰላም ባለቤትነታቸውን እንዲያሳዩ ፣ እምቅ አቅማቸውን እንዲያወጡና የድርሻቸውን እንዲወጡ በንቅናቄ መድረኮቹ ላይ የማስቻያ ሁኔታዎች እንደሚቀመጡ ተናግረዋል ።
አቶ አሰግድ ኃ/ጊዎርጊስ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት አሁን ላይ ሀገር እየመከረች ያለችበት ወቅት እንደመሆኑ ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታን የሚያገናዝብና የድርሻውን የሚወጣ ወጣት ለመፍጠር ወጣቱ ጋር ሰፊ ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ አንስተው በቀጣይ ቀናት በሁሉም ወረዳዎችና ብሎኮች ወጣቶችን በመለየት ውይይት የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል።
በከተማችን የሚከናወኑ ሀይማኖታዊ የአደባባይ በአላት ሰላማዊ ሆነው እንዲያልፉ የወጣቱ ድርሻ ትልቅ በመሆኑ ወጣቶች ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት የአካባቢን ሰላም በመጠበቅ እንዲሁም ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ የድርሻውን የሚወጣ ወጣት ለመፍጠርና በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ የወጣቶችን ተሳትፎ እንዲጎለብት፣ በወጣቶችና በመንግሥት መካከል ያለውን የጋራ መግባባትና ትብብር ለማጠናከርና የተሻለችና ሰላማዊ ከተማን ለመገንባት ያለመ የንቅናቄ መድረክ መሆኑን አቶ ክብረአለም ደምሴ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ መነሻ ዕቅዱን ሲያቀርቡ ገልፀዋል።
የወጣቶቹ የንቅናቄ መድረክም ከፊታችን ሀሙስ ጀምሮ እስከ ነሀሴ ሰላሳ በሁሉም ክ/ከተሞች ፣ ወረዳዎችና ብሎኮች ላይ የሚካሄድ መሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል።
ነሀሴ 12/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157