የጠንካራ የስራ ቡድን ግንባታ ለውጤታማነት እንደ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የጠንካራ የስራ ቡድን ግንባታ ለውጤታማነት እንደሚያበቃ በመረዳት በይበልጥ ተጠናክሮ በመስራት ውጤት ማስመዝገብ ይገባል።

የጠንካራ የስራ ቡድን ግንባታ ለውጤታማነት እንደሚያበቃ በመረዳት በይበልጥ ተጠናክሮ በመስራት ውጤት ማስመዝገብ ይገባል።

አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ 

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የዘጠና ቀናት ዕቅድ አፈፃፀምንና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ከሚገኙ የዘርፉ ባለሙያውች ጋር ውይይት አድርገዋል።

 አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ  እንዳሉት በ2018 በጀት አመት በዘርፉ በርካታ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን  አንስተው  ይህንን ስኬትና ውጤት ከላይ እሰከ ታችኛው መዋቅር በመናበብ የተሰራበት አግባብ መሆኑን ጠቁመው  በቀጣይም በይበልጥ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም ከፀጥታ ስራ አንፃር ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ወሳኝ መሰረት ነው ብለው የሀይማኖት ተቋማት የድርሻቸው እንዲወጡና በሰላም እሴት ግንባታ ላይ ሀይማኖታዊ አስተምሮን እንዲያጠናክሩ በቅርበት መሰራት እንደሚገባና እራስንም ለስራ ዝግጁ አድርጎ ማብቃትና ማሳመን  የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግና  ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ከባለፈው በጀት አመት በይበልጥ ጠንክሮ በመስራት ውጤታማ ስራ ማስመዝገብ ይገባልም ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ ብርሀኑ አያይዘውም ጠንካራ ቡድን ግንባታ ለውጤታማነት እንደሚያበቃ በመረዳት የለውጥና የመለወጥ ሰው በመሆን፣  ስራዎችን  በተገቢው መንገድ ሰርቶ በማስረከብ ፣ጠንካራ ቡድን በመገንባት ፣ ችግሮችን ከመሰረቱ በመፍታት መፍትሔ በጋራ በማመንጨት ግጭትን በተገቢው መንገድ መፍታት፣  ስኬቶችን ማስቀጠል ከስህተቶች መማር  ፣ አዲስ ክህሎት ማዳበርና የጋራ እሴቶችን በመገንባት ጊዜን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋልደ

የዘጠና ቀናት ዕቅዱንና የዘርፉን የ2019 ዓ.ም በጀት አመት የድርጊት መርሐ ግብር ዕቅድ ላይ በተመለከተ ገለጻ ያደረጉት አቶ ታጠቅ ነጋሽ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲያብራሩ ማዕድ ማጋራት፣የደም ልገሳ፣ ለአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት መርሐ ግብር ማስጀመር፣ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት ድጋፍ ማድረግ፣ሚዲያዎችንና ሌሎች ስልቶችን በመጠቀም የጽንፈኝነትና የጥላቻ ንግግር መግታት፣ለሀይማኖት አባቶች ስልጠና መስጠት፣የአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብር ማከናወን የሚሉት በዋነኝነት ሲገለጹ የ2019ዓ.ም ዕቅድ ተግባሮች ግቦችና በተጨማሪ ጥንካሬዎች የሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ በስፍት ተወያይተዋል።

ባለሙያዎቹ በበኩላቸው የዘጠና ቀናት ዕቅዶቹን በተገቢው መንገድ እያከናወኑ መሆኑን ገልጸው የቀጣይ አመት ዕቅዱን ተግባራዊ በማድረግ ስራዎችን በተገቢው መንገድም እንደሚያከናውኑ ገልፀዋል።

በመጨረሻም ዘርፉ በ2019 በጀት አመት ዕቅድ ካስኬድ በተደረገበትና ማውረድን በተመለከተ ከሰላም እሴትና የሀይማኖት ጉዳዮች  ከሁለቱም ዳይሬክተሮች ጋር እንዲሁም ከአስራ አንዱም ክ/ከተማ የዘርፉ አስተባባሪዎች ጋር የፊርማ ስነስርዓት አከናውነዋል።

ነሀሴ 11/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157