ተቋማትን በአፈፃፀም ዕውቅና መስጠትና ማበረታታት...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ተቋማትን በአፈፃፀም ዕውቅና መስጠትና ማበረታታት ለተሻለ የስራ ተልዕኮ ዝግጁ ማድረግ ነው።"

"ተቋማትን በአፈፃፀም ዕውቅና መስጠትና ማበረታታት ለተሻለ የስራ ተልዕኮ ዝግጁ ማድረግ ነው።" 

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ 

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ከማዕከል እስከ ወረዳ የተሻለ  አፈፃፀም  ላስመዘገቡ  ተቋማት ፣ ዳይሬክቶሬቶችና ባለሙያዎች ዕውቅናና ማበረታቻ ሽልማት ሰጠ።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በዕውቅና መርሀግብሩ ላይ እንዳሉት  ተቋማትን በአፈፃፀም ዕውቅና መስጠትና ማበረታታት ለተሻለ የስራ ተልዕኮ ዝግጁ ማድረግ ነው ብለው  ዛሬ ዕውቅና የተሰጣቸው የተቋም ኃላፊዎችና ሰራተኞች እንደ ስንቅ በመያዝ  በቀጣይ የተሻለ ለመፈፀም ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ገልፀዋል።

ቢሮው  ከመአከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ  የዘርፉ ተቋማትና ሰራተኞች የላፕቶፕ ፣ ዴስክቶፕ  ኮምፒውተር ፣ ስካነር ፣ ፕሪንተርና  ሰርትፍኬት ዕውቅናና ሽልማት  ሰጥቷል።

በዚህም :- 

1ኛ  አዲስ ከተማ እና ለሚኩራ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤቶች

 2ኛ የካ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት 

3ተኛ  ቂርቆስ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ከክ/ተሞች በደረጃ ተሸላሚ ሆነዋል።
 
ነሀሴ 9/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157