ቢሮው በ2019 በጀት አመት የፀጥታና የወንጀል መከላከልን ዕቅድን ካስኬድ በማድረግ ከቢሮው 4 ዘርፎችና ከክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤቶች ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ ።
ቢሮው በ2019 በጀት አመት የፀጥታና የወንጀል መከላከልን ዕቅድን ካስኬድ በማድረግ ከቢሮው 4 ዘርፎችና ከክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤቶች ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ ።
በፊርማ ስነ ስረዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት ቢሮው
ባለፈው በጀት ዓመት ካስመዘገበው ውጤት በይበልጥ በቀጣይ አመት ተጠናክሮ ውጤቶችን ለማስቀጠል የስምምነት ሰነዱ አስፈላጊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ስራዎችን ቆጥሮ በመስጠትና በመቀበል ለዘላቂ ሰላምን ማስፈን በመትጋት በተጨማሪ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች ላይ በትኩረት በመስራት ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ አሳስበው ከመንግሥት ምስረታ ጀምሮ በርካታ ኩነቶች በቀጣይ አመት ስለሚከናወነው ትኩረት በመስጠት ሰላምን ማስጠበቅ ይገባል ብለዋል።
ከመላው የከተማው ነዋሪ ጋር በሰላም በደህንት ጉዳዮች ላይ በማተኮር ከሸገር ከተሞች ጋር ቅንጅታዊ ስራዎችን ማጠናከር መልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራሮችን ከስር መሰረቱ በመንቀል ተቋምን በመገንባት የማህበረሰቡን አስተሳሰብና ልዕልናውን ከፍ በማድረግ በሚቻልበት በውይይት የሚያምን ማህበረሰብ መፍጠር ይገባል በማለት የህዝብ ለህዝብ ትስስሩን ማጎልበት ሀያ አራት ሰዓት የጸጥታ አጠባበቅ ስራዎችን ማጠናከርና ተደራሽነቱን ያላቀ ማህበረሰብ አቀፉ ፖሊሲዎችን ማስቀጠል ባጠቃላይ ቢሮውን በይበልጥ በሚገልጽ በልኩ አጠናክሮ በመስራት የከተማውን ሰላም ማጽናት ይጠበቅብናል ሲሉ ሀላፊዋ ተደምጠዋል ።
በመጨረሻም በቅርቡ የደንብ ማስከበር አማካሪና በምክትል ስራ አስኪያጅነት ተቋሙን የመሩት ወ/ሮ አበባ እሸቴ የህሊና ጸሎት መርሐ ግብር ተከናውኗል ።
ነሀሴ 9/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157