የተቋም ውጤታማነት ለማስቀጠል ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅራዊ ሪፎርምን ማጠናከር ፣ ህዝቡን የሰላም ባለቤት ማድረግና በቅርበት መሰራት እና ጠንካራ የፀጥታ ስምሪት መስጠት ይገባል።
የተቋም ውጤታማነት ለማስቀጠል ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅራዊ ሪፎርምን ማጠናከር ፣ ህዝቡን የሰላም ባለቤት ማድረግና በቅርበት መሰራት እና ጠንካራ የፀጥታ ስምሪት መስጠት ይገባል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
ይህን ያሉት በቢሮው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ምዘና፣የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ኦሬቴሽን መድረክ ላይ ሲሆን፣ በገለጻቸውም በ2018 በጀት ዓመት የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ የአመራር ጥንካሬ፣ የተቀናጀ የስራ አፈጻጸምና የኦፕሬሽን ስራዎች ወሳኝ ሚና እና በየአካባቢው ሊከሰቱ የሚችሉ ወንጀሎችን ቀድሞ በመለየትና በማክሸፍ የተሻለ ውጤት መመዝገብ መቻሉንም አንስተዋል።
ኃላፊዋ አክለውም ከሸገር ከተማ ጋር በጋራ የሚከናወኑ የሰላምና የፀጥታ ስራዎችም የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንና በተለይም የተቋማትን ትብብርና ቅንጅት ማጠናከር የሰላምና ፀጥታ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።
በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የቢሮው ዕቅዶች አፈጻጸም በየዘርፉ ተገምግሞ፣ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ የነበሩ ተሞክሮዎች፣ የታዩ ክፍተቶችና በቀጣይ መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች በጥልቀት የተዳሰሰ ሲሆን፣ የ2018 ዓ.ም. የስራ አፈጻጸም ምዘናው በተለይም የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ፣ የህግ ማስከበርን ለማጠናከር፣ የወንጀል መከላከልና ቁጥጥርን ለማሻሻል እንዲሁም ከህብረተሰቡና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የተፈጠረውን ትብብር በማጠናከር የተከናወኑ ተግባራት ላይ ትኩረት አድርጓል።
አቶ ማስረሻ ሀብቴ የዕቅድና በጀት ክትትል ግምገማና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ኦሬንቴሽን በመድረኩ ያቀረቡ ሲሆን፣የኦረንቴሽኑ ዋና ዓላማ የ2018 ዓ.ም. ልምድና ትምህርትን መነሻ በማድረግ ለ2019 በጀት ዓመት ግልጽ፣ ተግባራዊና ውጤት ተኮር ዕቅድ በማዘጋጀት የቢሮውን የሰላምና ፀጥታ ስራ ይበልጥ ማጠናከር ነው ብለዋል።
የ2019 ዓ.ም. ዕቅድ ላይ የወንጀል መከላከልና ህግ ማስከበር፣ የህዝብ ሰላምና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የህብረተሰብ ተሳትፎን ማሳደግ፣ የተቋማትን ቅንጅት ማጠናከር፣ የተቋም አቅምን ማሳደግና የስራ አፈጻጸምን በውጤት ለመለካት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ያካተተ ዕቅድ አቅርበዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች የ2018 ዓ.ም. አፈጻጸምን በጠንካራ ጎኖች ላይ በመመስረትና የታዩ ክፍተቶችን በማረም 2019 ዓ.ም. የሰላምና ፀጥታ ስራዎችን በተሻለ አቅም ለመፈጸም በቁርጠኝነት እንደሚሰሩና የ2018 በጀት ዓመት የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል፣ የተሻለ ተሞክሮዎችን በማስፋትና ከህብረተሰቡ ጋር በተቀናጀ መልኩ በመስራት የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ይበልጥ ለማረጋገጥ በጋራ እንደሚሰሩም ገልጸዋል።
ነሀሴ 9/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157