የወንጀል መንስኤዎችን በየአካባቢው በመለየት የቅ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የወንጀል መንስኤዎችን በየአካባቢው በመለየት የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራ በመስራትና ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የአካባቢንና የከተማን ሰላም በዘላነቂነት ማስቀጠል ይገባል።

የወንጀል መንስኤዎችን በየአካባቢው በመለየት የቅድመ ወንጀል  መከላከል ስራ በመስራትና ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ  የአካባቢንና የከተማን ሰላም በዘላነቂነት  ማስቀጠል ይገባል።

          ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ 
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ 
           
"የወንጀል መንስኤዎችና የመከላከያ መንገዶች ለሰላማዊ እና ደህንነቱ ለተጠበቀ ከተማ " በሚል ርዕስ  የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በጋራ በመሆን  አውደ ሰላም የተሰኝ የቶክ ሾው የውይይት መድረክ አካሂዷል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ    የቶክሾው መድረክ ማስጀመሪያ ላይ እንዳሉት የወንጀል መከላከል ስራ የሁል ጊዜ ስራ በመሆኑ  ትኩረት የሚሹ የፀጥታ ችግር ሉያስከትሉና የወንጀል መንስኤዎችን በመለየትና  ወንጀልን ለማስፋፋት ሌት ተቀን አቅደው የሚሰሩ ግለሰቦችና ቡድኖች  መከታተልና  ለህግ በማቅረብና የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም የፀረ ሰላም ሀይሎች   ወቅት እየጠበቁ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋላጎታቸውን በብጥብጥ በማጭበርበር  ለማሳካት የሚሰሩ ቢሆኑም የፀጥታ ተቋማት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የሰላም ማስጠበቅ ስራ እየሰራ መሆኑን አንስተው የወንጀል መንስኤዎችን በየአካባቢው  በመለየት ወንጀልን ቀድሞ በመከላከል ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ጠንካራ የጸጥታ ሀይሎችን መፍጠር   የከተማችንን ሰላምና ጸጥታ ዘላቂነት አስተማማኝ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ በመትጋትና በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ከተማችን አዲስ አበባ ደህንነቷ አስተማማኝ እንዲሆን ያደረገው አንዱ ለወንጀል መንስኤ የሆኑ ስጋቶችን ቀድሞ በጥናት በመለየት በመከላከል ብሎም ሀያ አራት ሰአት ጠንካራ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት በመዘርጋትና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ፈጣን ምላሽ አሰራሮች በመተግበር ረገድ ውጤታማ ስራዎች በመስራት ከተማችን በየወቅቱ ከሚታቀዱላት የጸጥታ ችግሮች እና የሽብር ሀይሎች እንቅስቃሴ በመታደግ የህግ የበላይነት የማስፈንና የህብረተሰቡን በሰላም ወጥቶ መግባት ላይ ውጤታማ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ  ኃላፊዋ ተናግረዋል።

 የወንጀል አስከፊነትና ጉዳቶችን ሲገልጹ በመንግሥትና በህዝብ የሚከናወኑ ታላላቅ የልማት ስራዎች ከግብ እንዳይደርሱ፣
የመልካም አስተዳደር እጦት እንዲሰፍንና በመንግሥትና በህዝብ መካከል መተማመን እንዳይኖር፣አብሮነትን መሸርሸር፣ወጣትና ሀገር ተረካቢ  ማሳጣት ብሎም በህጻናትና ሴቶች ላይ የከፋ ስነ ልቦና ተጽዕኖ ማሳደር፣ የመንግስት ፕሮጀክቶችና ገቢ ላይ እንቅፋት እንዲፈጠር  እንደሚዳርጉና እነዚህን ለመከላከል በትኩረት ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን  አብራርተዋል። 

አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትልና የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ወንጀልን ማጥፋት ባይቻልም መቀነስ እንደሚቻል አንስተው ህብረተሰቡ  ከፀጥታ ተቋማት ጋር በመተባበር ወንጀል ጠል ማህበረሰብ መፍጠር መቻል አለበት ብለዋል።

ዘርፍ ኃላፊው አክለውም  የወንጀል መከላከል ስራችንን በእጅጉ የሚያግዙ መሰረተ ልማቶች በመሰራታቸው በተጠንቀቅ ቆሞ ከተማውን እየጠበቀ የሚገኝ ማህበረሰብ አጋዥ የጸጥታ ሀይሎች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የከተማችን ህዝብ ወንጀል የሚፈጽሙ አካላት ላይ መረጃ በመስጠት ምስክር በመሆን አካባቢውን በመጠበቅና ከጸጥታ ሀይሉ ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ያለውን ስራ ማጠናከርና ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

የሰላምና ደህንነት ጥናት ረዳት ፕሮፌሰርና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ኢንስቲትዩት ኃላፊ ም/ል/ኮ/ር ዶ/ር መሳይ አሰገዶም፣ የወንጀል መንስኤዎች ስነ-ህይወታዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን እና የአዲስ አበባ የወንጀል መከላከል ተሞክሮዎችን በማጠናከር ረገድ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ምክረ ሐሳቦችን አቅርበዋል።

በመድረኩ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የአዲስ አበባና የሸገር ከተማ የጸጥታ ሀላፊዎች፣የሀይማኖት አባቶች ሀደ ሲንቂዎች አባ ገዳዎች ወጣቶች የሰላም ሰራዊቶች የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮችና ሌሎችም በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

ነሀሴ 7/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157