ደም በመለገስ የሰዎችን ሕይወት እንታደግ

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ደም በመለገስ የሰዎችን ሕይወት እንታደግ

"ደም በመለገስ የሰዎችን ሕይወት እንታደግ"

                 አቶ ብርሃኑ ረታ 

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊና የሃይማኖትና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ 

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች፣የሃይማኖት አባቶች  ደም ለገሱ።

 አቶ ብርሀኑ ረታ   የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የሀይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ በደም ልገሳ ላይ ተገኝተው  እንዳሉት  ቢሮው  ከዋና የስራ ኃላፊነቱ ባሻገር ለህብረተሰቡ የሚጠቅሙ የተለያዩ ሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በማከናወን ማህበራዊ ተግባራትን በመደገፍና በመሳተፍ የአንድነት፣ የመረዳዳትና የሰብዓዊነት እሴቶችን ለማጠናከር እየሰሩ እንደሆነም ገልፀዋል።

የደም ልገሳው የተካሄደው ህብረተሰቡ በችግር ጊዜ የሚያሳየውን መረዳዳትና የመተጋገዝ ባህል ለማጠናከር እንዲሁም በደም እጥረት ምክንያት ህይወታቸው ሊያሰጋ የሚችል ዜጎችን ለመታደግ በማሰብ የታለመ ነው።

በደም ልገሳው ላይ የተሳተፉ አካላት፣ ደም መለገስ አንድ ሰው ለሌላ ሰው ሊያደርገው ከሚችለው ትልቅ የሰብዓዊነት ተግባር አንዱ መሆኑን ገልጸው፣ ሌሎችም  የደም ልገሳን በማድረግ ደም ለሚፈልጉ ወገኖች ደም በመለገስ ህይወት ማዳን  እንዲችሉ  ጥሪ አቅርበዋል።

ነሀሴ 7/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

የሰላምና ፀጥታ መረጃዎችን ለማገኘት 👉

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157