የወንጀል መከላከል ስራ የህዝብን ግንዛቤ እና ንቃት በማሳደግ እንዲሁም ሌሎች ተደጋጋፊ እርምጃዎችን በመውሰድ የሚከናወን የቅድመ መከላከል ላይ ያተኮረ አሰራር ነው።"
"የወንጀል መከላከል ስራ የህዝብን ግንዛቤ እና ንቃት በማሳደግ እንዲሁም ሌሎች ተደጋጋፊ እርምጃዎችን በመውሰድ የሚከናወን የቅድመ መከላከል ላይ ያተኮረ አሰራር ነው።"
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
"አውደ ሰላም " ቶክሾው መድረክ ማስጀመሪያ ላይ የተናገሩት
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር በጋራ የሚያዘጋጀው "አውደ-ሰላም" የህዝብ ውይይት የቴሌቪዥን ፕሮግራም "የወንጀል መንስኤዎችና የመከላከያ መንገዶች ለሰላማዊ እና ደህንነቱ ለተጠበቀ ከተማ" በሚል ርዕስ በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።
መድረኩ በሀይማኖት አባቶችና ፣ በአባገዳዎችና ሀዴ ስንቄዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን በዚህ የቶክሾው ውይይት ላይ የወንጀል መንስኤዎችና የመከላከያ መንገዶች ለሰላማዊ እና ደህንነቱ ለተጠበቀ ከተማ በሚል የመወያያ ጥናታዊ ፅሁፍ በምሁራን ቀርቦ ሰፊ ውይይት ይደረጋል።
የውይይቱን ሙሉ መረጃ ይዘን እንመለሳለን!!
ነሀሴ 7/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
የሰላምና ፀጥታ መረጃዎችን ለማገኘት 👉
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157