የሀይማኖት ተቋማት ለኢትዮጲያኖች እርስ በርስ የ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የሀይማኖት ተቋማት ለኢትዮጲያኖች እርስ በርስ የሚያስተሳስሩ ገመዶች ናቸው።

የሀይማኖት ተቋማት ለኢትዮጲያኖች እርስ በርስ የሚያስተሳስሩ ገመዶች ናቸው።

አቶ ብርሀኑ ረታ 
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የሀይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ 

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ  በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ ስራ  የተለያዩ በጎ ፈቃደኛ የዕምነት ተቋማትን በማስተባበር የአቅመ ደካሞችን የመኖሪያ ቤት የማደስና የአብሮነትንና የእርስ በርስ መረዳዳትን ባህልና እሴት የማጠናከር ስራ እየሰራ ይገኛል። ዛሬም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤትና በማስተባበር የ5  አቅመ ደካሞችን የመኖሪያ ቤት ዕድሳት አስጀምሯል።

አቶ ብርሀኑ ረታ  የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የሀይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ  በመኖሪያ ቤት  ዕድሳት ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው እንዳሉት  የሀይማኖት ተቋማት ትውልድን ይገነባሉ ሀገርን ያፀናሉ በዚህም የእስልምና ተቋም  ሰላም እንደመሆኑ ሰው መሆንን በማስቀደም  ህዝብን በማስተሳሰር  እርስ በርስ የመረዳዳት እሴትን በማጠናከር ዛሬ ያስጀመረው የመኖሪያ ቤት ዕድሳት የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።  

ኃላፊው አክለውም ቢሮው የሀይማኖት ተቋማትን በማስተባበር በሁሉም ክ/ከተሞች  በዘንድሮው የክረምት ወቅት የ30 አቅመ ደካማ ቤቶችን ለማደስ ማስጀመሩን  አንስተው ዛሬ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተጨማሪ የ5 የአቅመ ደካማ  አባውራና እማውራ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት  በአጭር ጊዜ  አድሶ ለነዋሪዎች ለማስረከብ መጀመሩን ገልፀው ይህን በጎ ተግባር  ሌሎችም  እንዲከተሉ ገልፀዋል።

ኡስታዝ አብዱረዛቅ መሀመድ  የአ/ከተማ ክ/ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ እንደገለፁት እስልምና ሰው መሆንን በማስቀደም ማንኛውንም ዜጋ  የማገዝና የመርዳት ስራ እየሰራ መሆኑን አንስተው  ዛሬም በአ/ከተማ ክ/ከተማ የ5 እማውራና አባውራ አቅመ ደካሞችን ቤት ሙሉ በሙሉ አድሶ በአጭር ጊዜ ለማስረከብ መጀመሩን ተናግረዋል።

ነሀሴ 6/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

የሰላምና ፀጥታ መረጃዎችን ለማገኘት 👉

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157