የአቅመ ደካማ ዜጎችን የመኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ አድሶ በአጭር ጊዜ ለነዋሪዎች ለማስረከብ ዛሬ ተጀመረ።
የአቅመ ደካማ ዜጎችን የመኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ አድሶ በአጭር ጊዜ ለነዋሪዎች ለማስረከብ ዛሬ ተጀመረ።
በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ከእስልምና ሀይማኖት ተቋም ጋር በመተባበር የአቅመ ደካማ ዜጎችን የመኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ በአዲስ መልክ በአጭር ገንብቶ ለማሴረከብ ዛሬ በወረዳ 14 አስጀምሯል።
አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ በበጎ ተግባር መርሀ ግብሩ ላይ በመገኘት ተግባሩን ያስጀመሩት ሲሆን እንዲህ አይነት በኢኮኖሚ ዝቅተኛ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማገዝ በሰማይም በምድርም ትልቅ በረከት ያለው ነው ብለው የቤት ግንባታው በእስታንዳርዱ መሠረት ተሰርቶ በአጭር ጊዜ ለነዋሪዎቹ እንደሚተላለፍ ገልፀዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ ተስፋዬ በበኩላቸው በክ/ከተማው የአቅመ ደካማ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን በበጎ ፍቃደኞች ትብብር እየተሰራ መሆኑን አንስተው ይህ የኢትዮጲያውያን መገለጫ ነው ብለዋል። ኃላፊው አክለውም አገልግሎቱ በተያዘው የክረምት ወቅት ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ገልፀው ይህም ተግባር በዋናነት በእምነት ተቋማት መካከል ያለውን የመቻቻልና የመደጋገፍ ብሎም አብሮነትን የሚያሳይ ድንቅ ተግባር ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ዛሬ የተጀመረው የመኖሪያ ቤት ዕድሳትም በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለነዋሪዎቹ እንደሚተላለፍ ተገልጿል።
ነሀሴ 5/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
የሰላምና ፀጥታ መረጃዎችን ለማገኘት 👉
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157