የሰላምና የአብሮነት እሴቶችን ለማጠናከር ያለመ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የሰላምና የአብሮነት እሴቶችን ለማጠናከር ያለመ የጋራ የምክክር መድረክ ተካሄደ

የሰላምና የአብሮነት እሴቶችን ለማጠናከር ያለመ የጋራ የምክክር መድረክ ተካሄደ።
       
      ሰኔ 25/2018 ዓ.ም(PSAB)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ከአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች ጋር በ2018 በጀት ዓመት የሃይማኖትና እምነት ተቋማት አፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ የጋራ የግምገማና የምክክር መድረክ አካሂዷል። መድረኩ በ2018 በጀት ዓመት የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠልና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ፣ በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ አስተቃቀድ ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው።

  የሁሉም ክፍለ ከተሞች የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኘበት በዚህ መድረክ ላይ፣የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክትል ዋና ጸሐፊ ሼህ አብዱላሚን አህመድ ባደረጉት ንግግር፤ ጉባኤው በእምነት ተቋማት መካከል ያለው ትብብር እንዲጠናከር በማድረግ ከመንፈሳዊ ተልዕኮው ባሻገር በሰላምና በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የማስተባበር ሚናውን ሲወጣ መቆየቱን ገልጸዋል። አክለውም የሰላምና የስነ-ምግባር ሞራል ጉዳዮችን ይበልጥ ለማሳካት በአዲሱ መመሪያ መሠረት በክፍለ ከተሞች ያሉ ጉባኤዎችን በማጠናከር የእምነት ተቋማት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል።

የቢሮው ም/ምክትል ቢሮ ኃላፊና የሃይማኖትና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ በበኩላቸው፤ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በከተማዋ በሚሰሩ የሰላም፣ የልማት፣ የትብብርና የአብሮነት ሥራዎች ላይ አሻራውን በጉልህ ማሳረፉን ጠቅሰዋል። ኃላፊው በንግግራቸው እምነትና ሰላም የማይነጣጠሉ እሴቶች ስለሆኑ ተቋማቱ ማኅበረሰቡን በስነ-ምግባር በመቅረጽና ጽንፈኝነትን በመታገል የልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ረገድ የሚያከናውኑት ተግባር ለከተማችን ዘላቂ መረጋጋት መሠረት ነው  በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በቢሮው የሃይማኖትና እምነት ጉዳዮች ዳ/ዳይሬክተር አቶ ታጠቅ ነጋሽ የሃይማኖትና እምነት ተቋማትን የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ለ2019 በጀት ዓመት አመላካች የሥራ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።

በአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የክፍለ ከተማ መምሪያዎች ኃላፊ አቶ ለሜሳ ጉደታ በበኩላቸው ፤ የእምነት ተቋማት የሚሰሩትን ዋና ዋና ተግባራት ከመሠረቱ ጀምሮ የነበረውን ሂደት በሰነድ መልክ አቅርበዋል። ኃላፊው በቀጣዩ የክረምት በጎ አድራጎት ተግባራትና መሰል ማኅበራዊ ሥራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ የሰላም እሴት ግንባታን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በቀረቡት ጽሑፎችና ሰነዶች ላይ ከተሳታፊዎች ሰፊ ሐሳብና አስተያየት ተነስቶ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ መድረኩን በጥያቄና መልስ መሪነት የመሩት አቶ ብርሃኑ ረታ እና ሼህ አብዱላሚን አህመድ ለተነሱት ነጥቦች ማጠቃለያና የቀጣይ የጋራ ስምሪት አቅጣጫዎችን በመስጠት መርሃ-ግብሩ  ተጠናቋል።

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157