የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አሻራውን ለማሳረፍ የቅድመ ዝግጅት የጉድጓድ ቁፋሮ መርሐግብር አካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አሻራውን  ለማሳረፍ  የቅድመ ዝግጅት የጉድጓድ ቁፋሮ  መርሐግብር አካሄደ፡፡

ሰኔ   24/2018   ዓ.ም(PSAB)

የአዲስ አበባን የነገ ውበትና የሀገራችንን የአረንጓዴ ልማት ጉዞ ይበልጥ ለማፋጠን የሰላምና ጸጥታ መዋቅሩ በተግባር ግንባር ቀደምነቱን ማረጋገጡን ቀጥሏል።  ቢሮው በቀጣይ ሳምንት  ለሚያካሂደው የ2019 የክረምት ወራት ታላቁ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ቅድመ ዝግጅት  የተግባር ዘመቻ ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በከተማ አቀፍ ደረጃ 100,000 (አንድ  መቶ ሺህ)  ችግኝ  ለመትከል ዕቅድ የያዘ ሲሆን  ለዚሁ የሚሆን  የቅድመ ዝግጅት የጉድጓድ  ቁፋሮ ዕቅድ ይዞ ወደ ተግባር የገባ ሲሆን፤ ዛሬ የተካሄደው ታላቅ የጋራ ዘመቻ የዚሁ ዕቅድ አካልና መጀመሪያ ነው።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በቦሌ ቡልቡላ ልዩ ስሙ ሁሴን ግቢ በተባለው አካባቢ በተካሄደው በዚህ የጉድጓድ ቁፋሮ ዘመቻ ላይ  የቢሮው መዋቅር  ሁሉም ክ/ከተሞችን  በማሳተፍ  በጋራና በቅንጅት በነቂስ በመውጣት እያንዳንዱ ክፍለ ከተማ    የችግኝ መትከያ  ጉድጓዶችን በመቆፈር ለችግኝ  መትከያ ቦታ ዝግጁ ተደርጓል፡፡ 

እንደ ሀገር  ለተጀመረው  የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ስኬታማነት የጸጥታው መዋቅር የአንበሳውን  ድርሻ  እያበረከተ የሚገኝ ሲሆን  ከየክፍለ ከተማው የሰላምና ጸጥታ አደረጃጀት የተወጣጡ   በጎ ፈቃደኛ የሰላም ሰራዊት አባላት፣የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች፣የፓሊስ አባላትና አመራሮች በተሰጣቸው  ግልጽ የጉድጓድ  ቁፋሮ  ዕቅድ መሠረት  ግቡን ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል፡፡ 

የሰላም ሰራዊቱ አካባቢውን በንቃት ከመጠበቅ ባለፈ የቢሮውን ማዕከላዊ የልማት ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ ሁልጊዜም ግንባር ቀደም መሆኑን በተግባር እያሰየ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ውብና አረንጓዴ ለማድረግ በተያዘው ስትራቴጂክ ዕቅድ መሠረት፤ የጸጥታ መዋቅሩ የሰላም ዘብ ብቻ ሳይሆን የልማትም ዋልታ መሆኑን እያረጋገጠ ይገኛል። ዛሬ የተመዘገበው ደማቅ አፈጻጸም የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ሲሆን፣ ቢሮው የተሰጠውን የ100 ሺህ የጉድጓድ ቁፋሮ ዕቅድ 100% ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ችግኞችን እስከመትከልና እስከመንከባከብ ድረስ ያለውን ሰፊ ተግባር በሁሉም ክፍለ ከተሞች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የከተማችንን የጸጥታ መዋቅር በአረንጓዴ ልማትና በበጎ ፈቃድ ስራ ላይ እያሳየ ያለው ትጋት፣ የላቀ ቅንጅት እና ሀገራዊ አጋርነት በማስቀጠል የነገዋን አዲስ አበባ በአረንጓዴ አሻራችን ይበልጥ ለማድመቅ እንደሚሰራ ቢሮዉ ገልጿል።

ሰላም   ከሁሉም፣   በሁሉም፣   ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157