ወጣቶች በዲጂታል አውድ የሚገኙ መረጃዎች ወደ ምርታማነት በመቀየር የጋራ አብሮነትን በማጠናከር የሰላም አምባሳደርነታቸውን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።
ወጣቶች በዲጂታል አውድ የሚገኙ መረጃዎች ወደ ምርታማነት በመቀየር የጋራ አብሮነትን በማጠናከር የሰላም አምባሳደርነታቸውን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ
ሰኔ 23/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር በመተባበር "የወጣቶች ሚና ለዘላቂ ሰላም ግንባታ" በሚል ርዕሰ ከወጣቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር አውደ ሰላም የሰላም መድረክ ተካሄዷል።
በሰላም የወጣቶች መድረክ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ባስተላለፉት መልዕክት ሚዲያን በመጠቀም ከህዝብ ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ በማጠናከር በከተማዋ ሰላምና ደህንነት ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ ለመፍጠር እና ለሰላም እሴት ግንባታም ሆነ ለህግ የበላይነት መረጋጋት የከተማችን ማህበረሰብ ተሳትፎውንና የባለቤትነት ስሜቱን ማጎልበት ላይ መሰረት በማድረግ አውደ ሰላም በሚል ስያሜ በየወሩ እንደሚካሄድ ያስታወሱት ሀላፊዋ ሀገራችንን ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ስመ ገናና ከሆኑ አገራት ግንባር ቀደም ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይዘው የሚሻገሩት ታሪክና ትውፊት ያላት እንደመሆኗ መጠን ከዘመኑ ጋር አብሮ የመጓዝ የማይደፈር ቆራጥ ህዝብ ያላት ናትም ሲሉ ተደምጠዋል ።
የቢሮው ሀላፊዋ አያይዘውም ሀገራችን የብዙ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሚኖሩባት በመሆኗ ወጣቶች ልዩነቶችን በውይይት በመከባበር በመቻቻል እንዲሁም ከፍተኛ የሰላምና የበጎ ማህበራዊ አመለካከት የሚያዳብሩ ውይይቶች አቅም እንዳላቸውም አንስተው መልካም ዜጋ ለማፍራትና ሀገራችን የጀመረችውን ለውጥ ለማስቀጠል ብሎም ሁለንተናዊ ብልጽግናን እውን ለማድረግ የተሻለ ግንዛቤ እንዲይዙ በሀገራዊ እሳቤ እሴቶችን መላበስም ይገባቸዋል በማለት ተናግረዋል።
ዛሬን ላይ ቆመን ለነገ ጭምር በሚጠቅም መልኩ በተግባር በቁርጠኝነት እንዲሁም በድፍረት ዘላቂ ሰላም መገንባት ላይ ወጣቶች የማይተካ ሚና እንዲጫወቱ በማመን ወጣቶች የሰላም ተጠቃሚዎች ብቻ ሳይሆኑ ገንቢዎቹና ጠባቂዎቹ ስለሆኑ ሚናቸውን እንዲወጡ ማስቻል ይገባልም ሲሉ ክብርት ሀላፊዋ አሳስበዋል።
በመጨረሻም የወጣቱ ትውልድን የዘላቂ ሰላም ግንባታ ለሁለንተናዊ ልማት ያለውን አበርክቶ አጠናክሮ በማስቀጠል ለዓላማ ጠንክሮ በመስራት አዕምሮን በመቆጣጠርና በሰከነ መንፈስ ማሰብና ለሰላም መስራት ብሎም ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ጉዳዮች ቀድሞ በመራቅ ችግር ሲፈጠር በሰላም በምክክር የመፍታት ባህልን ማዳበር ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አደራ ጭምር አሳስበዋል ።
በሁሉም ተቋም የተቋሙንና የሃይማኖትን ካባ በመልበስ ብሔርንና ሃይማኖትን በማጋጨት ሳይሆን በመቻቻል ሁሉንም አንድ የሚያደርግ ሐሳቦችን በማምጣት ወጣቱን መገንባት አለበት ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ጥበቡ ተናግረዋል።
ሀላፊው አክለውም ወጣቱ ምክንያታዊ በመሆን በአእምሯቸው ውስጥ የተከማቸ ዕውቀት በመልካም ነገር እና በሁሉም ንቁ በመሆን በማስተማር ወጣቶች የሰላም አምባሳደር ሆነው መስራት አለብት ብለዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት ምሁራን ዶ/ር ታምሩ ፈይሳ እና ዶ/ር ጃራ ሰማ በበኩላቸው፣ ወጣቶችን ከሱስ እራሳቸውን በመጠበቅ ለሰላም ግንባታ አበርክቷቸውን ከፍ ማድረግ የሚያስችል ጥናታዊ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጓል።
ሰኔ 23/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት:- 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ
ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79