"ወጣቱ ትውልድ መዲናችንን ከዲጂታሉ ዘመን የሀሰ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

"ወጣቱ ትውልድ መዲናችንን ከዲጂታሉ ዘመን የሀሰት መረጃዎች ታድጎ የሰላም ግንባታ ዋልታ ሊሆን ይገባል!" -

"ወጣቱ ትውልድ መዲናችንን ከዲጂታሉ ዘመን የሀሰት መረጃዎች ታድጎ የሰላም ግንባታ ዋልታ ሊሆን ይገባል!" -

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ 

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (AMN) ጋር በጋራ የሚያዘጋጀው "አውደ-ሰላም" የህዝብ ውይይት የቴሌቪዥን ፕሮግራም፣ "የወጣቶች ሚና ለዘላቂ ሰላም ግንባታ" በሚል ርዕስ በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ ወጣቱ በአዲስ
አበባ ሁለንተናዊ የልማትና የሰላም ጉዞ ውስጥ ያለውን የማይተካ ሚና አብራርተዋል።

ኃላፊዋ በንግግራቸው፣ "አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካውያን እና የዓለም አቀፍ ተቋማት መዲና ናት። የዚህች ከተማ ሰላም በዋናነት የሚረጋገጠው ደግሞ ቁጥሩ ከፍተኛ በሆነው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ነው። ዛሬ በምንገኝበት የዲጂታል ዘመን (Post-Truth Era)፣ ማህበራዊ ሚዲያው ወጣቱን ወደተሳሳተ አቅጣጫ ለመምራት ትልቅ መሳሪያ እየሆነ መጥቷል። በመሆኑም ወጣቱ እውነትና ሀሰትን በመለየት፣ ስሜታዊነትን በማስወገድ የከተማችን የሰላም ዘብ ሊሆን ይገባል" ብለዋል።

አክለውም፣ ዛሬ በከተማችን እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማቶች እና የስማርት ሲቲ ፕሮጀክቶች የወጣቱ አሻራ ያረፈባቸው መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ወጣቱ የሰላም ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን፣ አምባሳደርና ጠባቂ መሆን እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት ምሁራን ዶ/ር ታምሩ ፈይሳ እና ዶ/ር ጃራ ሰማ በበኩላቸው፣ ወጣቶችን ከሱስና ከተሳሳቱ አመለካከቶች
በማራቅ እንዴት በሀገር ግንባታ ላይ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ  እንደሚቻል ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበው፣ ከተጋበዙ ወጣት የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ፊት-ለፊት ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

ሰኔ 23/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት:-  8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ

ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79