የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ የድህረ ምርጫ የፀጥታ አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫን አስቀመጠ።
የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ የድህረ ምርጫ የፀጥታ አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫን አስቀመጠ።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የድህረ ምርጫ የፀጥታ ስራ ያለበትን ደረጃ በመገምገም በቀጣይ ትኩረት በሚሹ የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ አቶ ጌታሁን አበራ በምርጫው ወቅት የታየው የተቀናጀ አሠራርና የቅድመ መከላከል ስራዎች ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰው ይህንኑ መልካም ተሞክሮ በመውሰድ በቀጣይም አስተማማኝና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የድህረ ምርጫ ስራችንን በስምሪት አሰጣጥና የወንጀል መከላከል ስራዎች ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ የገለፁት አቶ ጌታሁን የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ በቁርጠኝነት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት በቅድመ ምርጫና በምርጫ ወቅት የታየውን ስኬታማነት ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበው በተለይም የህዝቡን የሠላም ባለቤት ማድረግ የሰላም ሠራዊት ስምሪቱን ማጠናከርና ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ጉዳዮችን በመከታተል ህግ የማስከበር ስራን ማጠናከር እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አህመድ ሀሰን እንደገለፁት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ መዋቅሩና የኮማንድ ፖስቱ አባላት ከፍተኛውን ድርሻ መወጣታቸውም ጠቁመው አሁን ላይም በድህረ ምርጫ የፀጥታ ስራ በተጠናከረና በተቀናጀ የአመራር ስምሪት መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አራጌ እሸቴ የፀጥታ ኮማንድፖስቱ ከፀጥታ አካሉ ጋር በጥምረት በመስራቱ አስተማማኝ የሆነ የፀጥታ ሁኔታን መፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል።
ኮማንደሩ አክለውም በቀጣይም የወንጀል መከላከል ሥራዎችን ይበልጥ በማጠናከር የሕዝቡን የደህንነት ስጋቶች ለመቅረፍ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ተናግረዋል።
ሰኔ 22/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት:- 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ
ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79