የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራትና የሲሲቲቪ ካሜ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራትና የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማ የተግባር ሂደትን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምልከታ ተደረገ።

የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራትና የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማ የተግባር ሂደትን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምልከታ ተደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው ዘላቂ ሰላም እንዲኖርና የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የነዋሪውን በሰላም ወጥቶ መግባት ለማረጋገጥና የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት በመሆን የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራትና የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማ  በማድረግ ነዋሪው ያለፀጥታ ስጋት ወጥቶ መግባት እንዲችል እየሰራ እንደሆነ ኮሚቴው ተዘዋውሮ በጎበኘበት ወቅት ተመልክቷል።

ክብርት ወ/ሮ  ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በማልከታው ወቅት  እንዳሉት  ከተማችንን ስጋት ውስጥ የሚጥሉ ጉዳዮችን በማክሸፍ  የወንጀልን እንቅስቃሴን መቀነስ  የተቻለው የሰላም ሰራዊቱ በተቀናጀ መልኩ  ከመደበኛው የፀጥታ ሀይል  ስምሪት በመውሰድ የተሰራው ጠንካራ ስራ ውጤት ነው ብለዋል።

ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም በዛሬ ምልከታ በታየው አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ላይ  ተግባሪ የተደረገው የወንጀል መከላከል ስራ ላይ አመርቂ ስራ መሰራቱንና ሌሎችም እንደ መልካም ተሞክሮ መውሰድ እንደሚገባ አስቀምጠው  አሁን ላይ ወቅቱ ክረምት እንደመሆኑ ብሎም ከፊታችን የመንግስት ምስረታ ትልቅ ሀገራዊ አጀንዳ እንደመኖሩ  ከወትሮው በበለጠ የፀጥታ ስምሪት ስራችን በማጠናከርና የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራቶች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ፣ የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማ ተግባራዊነትን በማጠናከር  በከተማችን አሁን ላይ ያለውን ሰላምና የወንጀል ምጣኔ መቀነስን ማስቀጠል እንደሚገባ በአፅንኦት አሳስበዋል።

የመኖሪያና የንግድ  አካባቢዎችን የውስጥ ለውስጥ መንገድ መብራት እንዲኖራቸውና በብርሀን እንዲሞሉ በመደረጉ በክ/ከተማው የወንጀል ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉን የገለፁት አቶ ታረቀኝ   ወርቅነህ   የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ  በከተማችን ንፁህ የሰላም አየር  እንዲኖርና ነዋሪው ያለምንም የፀጥታ ስጋት መንቀሳቀስ እንዲችሉ ማድረግ ተችሏል ብለው ይህ መሆን የቻለው የሰላም ሰራዊቱ ከመደበኛ የፀጥታ አካሉ ጋር በቅንጅት መስራት በመቻሉ መሆኑን  አብራርተው ነዋሪው በፀጥታና በቅድመ ወንጀል መከላከል ስራ ላይ ተሳትፎውን እንዲቀጥል ማድረግ ይገባል ብለዋል  ።

በምልከታው የተሳተፉ  የመብራት አስበሪ፣ የካሜራ  ገጠማ  እና ሞዴል ፖሊስ ማዕከላት ቁጥጥር   ኮሚቴ  በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የታየው የወንጀል ቅነሳና የፀጥታና ደህንነት ስራን ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ የሚያስደስትና ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆን መሆኑን አንስተው በተለይም በመርካቶ አካባቢ የተሰራው የመብራት ማስበራትና የካሜራ ገጠማ ስራ  አበረታች መሆኑን አብራርተው ይህን ሌሎችም ተሞክሮውን መውሰድ እንዳለባቸው አመላክተዋል ።

ሰኔ 20/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት:-  8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ

ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79