የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አስበሪ፣ የካሜራ ገጠማ እና ሞዴል ፖሊስ ማዕከላት ቁጥጥር ኮሚቴ አፈፃፀሙን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አስበሪ፣ የካሜራ ገጠማ እና ሞዴል ፖሊስ ማዕከላት ቁጥጥር ኮሚቴ አፈፃፀሙን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጠ።
በግምገማው ወቅት የመንገድ መብራትና የካሜራ ገጠማ ስራ በ11ዱም ክ/ከተሞች ያለው የትግበራ ሂደት የያዘ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በግምገማውም ውጤታማ መሆኑን ተመላክቷል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊና የኮሚቴው ሰብሳቢ እንዳሉት የፀጥታ ስራን ማጠናከር ሲቻል ሰላሟ የተረጋገጠባት ከተማን መፍጠር እንደሚቻል ጠቁመው የዜጎችን የደህንነት ስጋት ለመቀነስና ለህዝቦችን ሰላም መረጋገጥ ሁሉን አቀፍ የፀጥታ ስራ መስራት ይጠበቃል ብለው አሁን ላይ ከዚህ በተሻለ መስራትና በተለየም የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራት ፖሎችን መቀየርና መስራታቸውን መከታተል ያጠበቃል ብለዋል።
አክለውም ከተማችን አዲስ አበባ በፈጣን የዕድገት ጎዳና ላይ እንደመሆኗ ከተማዋን የሚመጥን የፀጥታ ስራ መስራት እንደሚገባ
አሳስበው በተለይም የኮሚቴው አካላት የሰላምና ፀጥታ ፣ የደንብ ማስከበር፣ የፖሊስ አካላት ፣ የመብራት አገልግሎት በቅንጅት ለውጤታማነቱ በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንዳሉት ኮሚቴው ስራዎችን በየጊዜው እየገመገመና ድጋፍ እያደረገ በመምጣቱ ዛሬ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የታየው ለውጥ ያመላክታል ብለው በቀጣይም አጠማክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ የአፈፃፀም ሪፖርቱን ሲያቀርቡ እንዳሉት በክ/ከተሞች ላይ እየተከናወነ ያለው የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራትና የካሜራ ገጠማ ስራ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ የወንጀል ምጣኔን መቀነስና የህብረተሰቡን በሰላም ወጥቶ መግባት ማረጋገጥ ብሎም የከተማዋን ሰላም ማረጋገጥ መቻሉን አብራርተዋል።
ሰኔ 20/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት:- 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ
ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79